ዳግማዊ ቶማስ ሳንካራ፤የአፍሪካው ቼኩቬራ በሚል ተቀጽላ ስሞች እየተሞካሹ የሚጠሩት ፕሬዜዳንት ኢብራሂም ትራውሬ ከአዲስ የግድያ ሙከራ መትረፋቸው ተሰማ፡፡ ፕሬዜዳንቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የአሁኑን የግድያ ሙከራ ሳይጨምር ለ18 ጊዜ ያህል ኢላማ ተደርገው ተርፈዋል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ የግድያ ሙከራዎች ጀርባ ፈረንሳይ እና ሌሎች የምዕራቡ ዓለም ሀገራት እጃቸው እንዳለም ይነገራል፡፡ ፕሬዜዳንት ኢብራሂም ትራውሬ ቡርኪናፋሶን በሁለት ዓመት ውስጥ ሊታመኑ የማይችሉ ልውጦችን እንድታይም አድርጓታል፡፡
ወደ ስልጣን እንደመጡ የወሰዷቸው እርምጃዎችም በእሳቸው ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎች እንዲደረጉባቸው በር ከፋች ሆነዋል፡፡
ካፒቴን ኢብራሂም ትራውሬ ከሁለት ዓመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በፈረንሳይ፡በእንግሊዝ እና በአሜሪካ መንግስታት ላይ እያራመዱት ባለው አቋም ጥርስ ውስጥ ገብተዋል፡፡
በተለይ የቡርኪናፋ ቀኝ ገዥ የነበረችው ፈረንሳይ ለዘመናት በሀገሪቱ ላይ የነበራትን ጥቅም በፕሬዜዳንት ኢብራሂም ትራውሬ አመራር እንድታጣ መደረጉ ፈረንሳይ ፕሬዜዳንቱን በህይወት ወደ መፈለግ እንድታመራ አድርጓታል ይባላል፡፡ በዚህ የተነሳም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥም የአሁኑን ሳይጨምር ከ18 ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርገዋል፡፡
ትላንትም የ36 ዓመቱን ፕሬዜዳንት ኢብራሂም ትራውሬን ለመግደልና መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ያለመ ሴራ መክሸፉ ተነግሯል፡፡
ፕሬዜዳንቱን በመግደል መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ በታሰበው ሴራ በርካታ የሀገሪቱ ወታደራዊ አባላትን ያካተተ ስለመሆኑ የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና ይፋ አድርገዋል፡፡
በዚህ የግድያ ሴራ ውስጥ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች ተሳታዎች መሆናቸውን የደህንነት ሚኒስቴር ተቋሙ የሁለቱን ግንኙነት በመጥለፍ ሴራውን ማክሸፉን ነው ያስታወቀው፡፡
በፕሬዜዳንቱ ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግስት ከቀናቶች ቀደም ብሎ በሚያዚያ 8 ለማድረግ ታስቦ እንደነበርም የደህንነት ሚኒስቴር ተቋሙ ገልጻል፡፡ ከዚሁ ጋር በተገናኘ የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ 9 ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸው ሲነገር ጥቂተ የማይባሉ ደግሞ ወደ ኮትዲቫር ሸሽተዋል ተብሏል፡፡
ፕሬዜዳንቱን ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፎች በፈረንሳይና በጣሊያን ከዚህ ቀደም መደረጋቸውን እናስታውሳለን፡፡ ይህ አልሳካ ሲላቸው ለእስላማዊ ጅሃዲስት ታጣቂዎች ገንዘብ በመክፈል ፕሬዜዳንቱን ለመግደል ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የቡርኪናቢ ወጣት ሲሻል ሚዲያ አክቲቪስቶች ገልጸዋል፡፡
ወጣቶቹ ይህ መሆኑ ቢያበሳጨንም ፕሬዜዳንታችን ምንም አለመሆናቸው ደግሞ ጥሩ ዜና ነው፡፡ እናም ለቡርኪናፋሶ እና ለፕሬዜዳንታችንን መጸለያችንን እንቀጥል የሚሉ ይዘቶችን ሲጋሩም ተመልክተናል፡፡

