ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነገሮች አሁን ከምናያቸው በላይ ሊከፉ እንደሚችሉ ተናገሩ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነገሮች አሁን ከምናያቸው በላይ ሊከፉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ትቀንሳለች የሚል እምነት እንደሌላቸውም ይፋ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ኢራን በቀጠናው ላይ ባሉ የአሜሪካ ንብረቶች ላይ ኢላማ ካደረገች አይታው የማታውቀው መዘዝ እንደሚጠብቃትም ትወቀው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነዋሪዎች ከኢራን ዋና መዲና ለቀው እንዲወጡ ካዘዙ በኋላ ነዋሪዎች ከከተማዋ ለቀው እየወጡ እንደሆነ እየተሰማ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ 17 ሚሊዮን የሚደርሰውን የቴህራን ከተማ ነዋሪን በሙሉ ለቃችሁ ውጡ የሚል ትዕዛዝ ትላንት ማምሻውን አስተላልፈዋል፡፡

እስራኤል ከዋና ከተማዋ አንዱን እና ከ300ሺ በላይ ህዝብ ያያዘውን ወረዳ ኢራናዊያን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ ካቀረበች በኋላ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የለም ሁሉም ሰው ከቴህራን ለቆ ይውጣ ማለታቸው ነው የተሰማው፡፡

በዚህ ስዓት ነዋሪዎች ከቴህራን ለቀው እየወጡ መሆኑን ከአገሪቱ የሚወጡ ምስሎች አሳይተዋል፡፡

በመዲናዋ የሚገነው ካራጅ ቻሉስ የተሰኘው ጉዳና ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እያቀኑ ባሉ መኪኖች መጨናነቁን አሳይቷል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል የኢራኑን መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒን ለመግደል የነበራትን ዕቅድ ውድቅ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ሆኖም እስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታናሁ ጉዳዩን እያጤኑበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሆሚኒ ግድያ ግጭቱን ይቋጨዋል እንዲሁም የኒውክሌር ጦርነትን ይከላከላል የሚል ግምት እንዳለቸው ከኤቢሲ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን የማበልጸግ መብት እንዳላት በተደጋጋሚ የሚናገሩት የኢራን ረጅም ጊዜ መሪ አያቶላህ አሊ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ጥያቄ ፈጥሯል፡፡

ከመካከለኛው ምስራቅ የሚወጡ መረጃዎች የሁለቱ አገራት ውጥረት እየተባባሰ መሆኑን ነው እያሳዩ የሚገኙት፡፡ እስራኤል በቀጥታ ሲተላለፍ በነበረ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሦስት ኢራናዊያን ስለመገደላቸው ተነግሯል፡፡

እስራኤል በቀጥታ ሲተላለፍ በነበረው መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ሚዲያው ይፋ አድርጓል፡፡

ቀደም ሲል በኢስላሚክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኢራን ብሮድካስቲንግ በተፈጸመው ጥቃት አንድ አዘጋጅና አንድ ሠራተኛ መገደላቸውን የኢራን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አሰራጭተዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በቴህራን በሚገኘው መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ማዕከል ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው የቀጥታ ፕሮግራም እየተላለፈ በነበረበት ወቅት ነው፡፡

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅትም ስርጭቱ ሲስተጓጎል እና ዜና ስታቀርብ የነበረች ጋዜጠኛም ከመቀመጫዋ ላይ ደንግጣ ስትነሳ እና ስትጮህ ታይቷል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቡድን 7ን ጉባኤ አቋርጠው መመለሳቸው ከተኩስ አቁም ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ እየተካሄደ የነበረውን የቡድን 7 ጉባኤ ከመጠናቀቁ በፊት አቋርጠው የተመለሱት በኢራንና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ላይ ለመስራት ነው የሚለውን መረጃ አጣጥለውታል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ትራምፕ ዋሽንግተን ቀደም ብለው የተመለሱት በተኩስ አቁም ላይ ለመሳተፍ ነው ማለታቸው ስህተት ነው ሲሉ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ አጋርተዋል፡፡

ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም እንደሚፈልጉ ይፋም አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም እውነተኛ ፍጻሜን እንደሚፈልጉ ለጋዜጠኞች መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ እንደማይፈልጉ ገልጸው ኢራን ኒውክሌር ማበልጸጓን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ኢራን የኒውክሌር መሳሪያ ሊኖራት አይችልም ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ በተጨማሪም እስራኤል በኢራን ላይ እየፈጸመች ያለውን ጥቃት ትቀንሳለች ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት ትረዳላችሁ፡ታውቃላችሁ፡እስካሁን ድረስ የቀነሰ የለም ብለዋል፡፡ ኢራን በቀጠናው ባሉ የአሜሪካ ንብረቶችን ኢላማ ካደረገች ከፍተኛ መዘዝ እንደሚጠብቃትም አስጠንቅቀዋል፡፡

ዛሬ ማለዳውን ኢራን ቴል አቪቭ፡ሃይፋ እና ሌሎች የእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎችን በአዳዲስ መሳሪያዎች እና በመቶ በሚቆጠሩ ድሮኖች እያጠቃች እንደሆነ የአገሪቱ ምድር ጦር አዛዥ ማስታወቃቸው ተሰምቷል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe