ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ ዓርብ ይከፈታል ቢሉመ ሙሉ በሙሉ መቼ እንደሚከፈት ግልጽ አይደለም ተባለ

በዚህ ስዓት ደግሞ በከፊል ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን እንዴት መቼ ሰርጡ ሙሉ በሙሉ ይከፈታል በሚለው ላይ ግን አሁንም ግራ መጋባቶች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

የዓለም መሪዎች ይህንን ስምምነት በመልካም የተመለከቱት ሲሆን፤በኢራን በኩል በተወሰነ መጠን ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ኢራን የሊባኖሱ ጦርነት እንዲቆም እየጠየቀች ሲሆን፤እስራኤል ግን የጦር ሃይሏ በሊባኖስ ያልጨረሰው የቤት ስራ ስላለው ይቆያል ብላለች፡፡

በርግጥ አሜሪካ እና ኢራን ላለፉት ወራቶች የመካከለኛው ምስራቅን አዲስ ገጽታ የሰጠውን ጦርነት በስምምነት ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል፡፡

ለወራቶች ተዘግቶ የነበረው ሆርሙዝ አርብ ከሚከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት በኋላም ሙሉ በሙሉ ክፍት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ የፊታችን ዓርብ ከኢራን ጋር በጄኒቫ የሚደረገው የፊርማ ስነ-ስርዓት በምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲቫንስ እንደሚመራም ታውቋል፡፡

አሜሪካ የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ ያለምንም ክፍያ እንዲያልፉ የምትፈልግ ሲሆን፤በሌላ በኩል ኢራን ደግሞ በሰርጡ በኩል የሚያልፉ የንግድ መርከቦች የማሪታይም ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል እያለች ነው፡፡

በጂ7 ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈረንሳይ የገቡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስምምነቱ ዝርዝር ነጥቦች በመጪዎቹ ቀናት ይፋ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

ኢራን አሁንም ቢሆን የሚደረሰው ስምምነት ሊባኖስን የሚያጠቃልል መሆን እንደሚገባው ታነሳለች፡፡ ምንም እንኳን ኢራን ይህንን ብትልም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ግን የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢራን የወደሙባትን የኒውክሌር መሠረተ ልማቶች መልሳ እንድትጠግን መፈቀድ የለበትም ብለዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe