ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከግድያ አዳንኳቸው ያሉት የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒ በቀጥታ የግድያ ኢላማ ሊደረጉ እንደሚችሉ ተሰማ፡፡ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ከጦርነቱ በኋላ በግልጽ ይህንን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
እስራኤል በ12 ቀናት ጦርነቱ ወቅት እንዲገደሉ ያላደረኳቸውን የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒን ምንም አይነት የስጋት ምልክት ካየሁ ላስወግዳቸው እችላለሁ ስትል ዝታለች፡፡
ከወደ ኢራን በኩል ለሚመጡ የትኛውም አይነት የደህንነት ስጋቶች ምላሻቸው የሚሆኑት ግለሰባዊ ጥቃቶች እንደሚሆኑ መከላከያ ሚኒስትሩ በግልጽ ተናግረዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ አሁን ከወደ ኢራን በኩል ስጋት ከተመለከትን በቀጥታ ክንዳችንን የምናሳርፈው በአያቶላህ አሊ ሆሚኒ ላይ ነው ብለዋል፡፡ በ12ቱ ቀናት ጦርነት ውስጥ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠቅላይ መሪውን ከግድያ እኔነኝ ያተረፍኳቸው በማለት ገልጸው ነበር፡፡ አሁን እስራኤል ሳይንቲስቶችን እና ሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሙያዎችን ኢላማ ከማድረግ የተሻገረ የግድያ ኢላማ እንዳላት እስራኤል ካትዝ በይፋ ተናግረዋል፡፡ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለሰላማዊ መንገድ ማበልጸጓን እንደማታቋርጥ በመግለጽ ላይ ነች፡፡ ሰሞኑንም በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ አገሪቱ ከአውሮፓ አገራት ዲፕሎማቶች ጋር እየመከረች ነው፡፡ ይህ ምክክር የማይሰምር ከሆነ ደግሞ የአውሮፓ አገራት በኢራን ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ይጠበቃሉ፡፡//

