የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሰጡት ድንገተኛ መግለጫ አሜሪካን አጥብቀው ወቅሰዋል! ‘በገንዘባችን የገዛነውን ሚሳኤል እንኳን አሜሪካ ልታስረክበን አልፈቀደችም’ ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
ከአሜሪካ የሚላከው የፓትሪዮት ሚሳኤል ቁጥር አጅግ ቀነሰ!
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከብሉምበርግ (Bloomberg) ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እንደገለጹት፤ አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ለዩክሬን እያቀረበች ያለችው በወር 12 የፓትሪዮት (Patriot) የአየር መከላከያ ሚሳኤሎችን ብቻ ነው። ይህም ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ወቅት ይላክ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በአራት እጥፍ ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል።
ገንዘቡን ከፍለናል ነገር ግን አሜሪካ አልፈቀደችውም!’
ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ነገር፤ ዩክሬን በ PURL ፕሮግራም አማካኝነት የባሊስቲክ ሚሳኤል መከላከያዎችን አስቀድማ በገንዘቧ የገዛች ቢሆንም፣ ዋሽንግተን ግን የመሳሪያዎቹን ማስተላለፍ አዘግይታዋለች።
ዘለንስኪ ሲናገሩ፦ “ለጦር መሳሪያዎቹ ክፍያ ፈጽመናል። የአሜሪካ ወገን የተወሰነውን አጽድቆ የቀረውን ግን ከልክሏል። ይህ ደግሞ በቴክኒክ ምክንያት የሆነ ሳይሆን የፖለቲካ ውሳኔ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዩክሬን ከተሞቿን እና የመሰረተ ልማት አውታሮቿን ከሩሲያ ሚሳኤሎች ለመጠበቅ ስትል ለዋሽንግተን አንድ ስምምነት አቅርባ ነበር። ይኸውም፦ “ዩክሬን የሩሲያን የዲዜል ማጣሪያ እና ማምረቻ ተቋማት ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ከተፈለገ፣ አሜሪካ በበኩሏ የፓትሪዮት ሚሳኤሎችን እንድታቀርብልን” የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ ስምምነትም ቢሆን አሁንም ምላሽ አላገኘም።
ዩክሬን ከአውሮፓ ህብረት ትልቅ የፋይናንስ ድጋፍ አግኝታለች፦ መስከረም ወር ላይ ዩክሬን ለ2026–2027 ከተመደበው የ90 ቢሊዮን ዩሮ የድጋፍ ብድር ውስጥ 3.2 ቢሊዮን ዩሮ ያህሉን ለፓትሪዮት ሚሳኤሎች ግዢ እንድታውለው ተፈቅዶላታል።
በአጠቃላይ የአውሮፓ ኮሚሽን 6.1 ቢሊዮን ዩሮ የአየር መከላከያ ሚሳኤሎችን (በአሜሪካ የተሰሩ PAC-3 ሚሳኤሎችን ጨምሮ) እና ድሮኖችን ለመግዛት አጽድቋል።
የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር እንደገለጹት፣ ዩክሬን ከእነዚህ የአውሮፓ ብድሮች በሚገኝ ገንዘብ አጠቃላይ 1,000 የሚሆኑ የፓትሪዮት ሚሳኤሎችን ለማዘዝ ውል ተዋውላለች። ነገር ግን አብዛኞቹ ሚሳኤሎች የሚደርሱት በሚመጡት ዓመታት ውስጥ ይሆናል።
ጀርመን ባለፈው ሰኔ ወር 400 ሚሊዮን ዶላር መድባለች
ብሪታንያ፦ በ መስከረም ላይ የ100 ሚሊዮን ፓውንድ የአየር መከላከያ ፓኬጅ ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም የፓትሪዮት ሚሳኤሎችን፣ የመድፍ ጥይቶችን እና ድሮኖችን ያካተተ ነው።
“ዩክሬን በጦርነቱ መሀል ሆና በገንዘቧ የገዛቻቸውን መሳሪያዎች ለማግኘት አሁንም በአሜሪካ ውሳኔ ወድቃ ትገኛለች።//
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሜሪካንን አጥብቀው ወቀሱ

