ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ፑቲን ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት አስጀምረውታል አሉ

ፕሬዝዳንቱ ዩክሬን አራት ዓመት የደፈነውን ጦርነት በድል አድራጊነት እንደምታጠናቅቅ እምነት እንዳለቸውም ጠቁመዋል፡፡
ፑቲን ያስጀመሩት የሦስተኛው የዓለም ጦርነትን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ በፑቲን ላይ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደር ነው ብለዋል፡፡
ሩሲያ አሁን በእጇ ስር ስለሆነው እና እስከመጨረሻው ተላልፎ እንዲሰጣት ስለጠየቀችው 20 በመቶ በላይ የሚሆነው የምስራቃዊ ዩክሬን ግዛት እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱ መሬቶችን በተመለከተ የተኩስ አቁምን እስካስገኘ ድረስ ለምን አትስማሙም የሚል ጥያቄ ቢቢሲ አቅርቦላቸዋል፡፡
ይህ ድርጊት በዚያ የሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦቻችንን እንደመተው ነው የምመለከተው ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ጥያቄ መመለሱ ብቻውን የፑቲንን ፍላጎት በዘላቂነት ያሟላል የሚል እምነት እንደሌላቸውም ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ሞስኮ እና ኪቭ በዋሽንግተን አሸማጋይነት በጄኔቫ ያለውጤት የተጠናቀቀ ድርድር ማካሄዳቸው አይዘነጋም፡፡
በዚያው ሰሞንም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩክሬን በፍጥነት ወደ ድርድር ጠረጼዛው መምጣቱ ይሻላታል ብለው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፑቲንን ማስቆም ለመላው ዓለም ድል ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውየው በዩክሬን ብቻ አያቆምም በማለት ገልጸዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe