ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ እንዴት ሞቱ?

(ቁም ነገር ሚዲያ ነሀሴ 26 ቀን 2016)የአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ከ10 ቀናት በፊት ነበር ለሞት ያበቃቸው ድንገተኛ አደጋ በመኖሪያ ቤታቸው ያጋጠማችው፡፡ ፕሮፌሰር ሁሌም እንደሚያደረጉት ቀኑን ሙሉ ሳሎን ቢታችው ውስጥ ሆነው የተለያዩ መጻህፍትን ሲያነቡ ቆይተው ሲመሽ ከራት በኋላ ወደመኝታ ቤታችው ይገባሉ፤

ለወትሮው እንደሚያደረጉት መኝታ ቤት ገብተው አልጋ ላይ ሆነው መጽሃፍ የማንበብ ልምድ ስላላቸው አጠገባቸው ያለው ኮሞዲኖ ላይ ሻማ ለኩሰው ማንበበ ይጀምራሉ፤ ሆኖም እንቅልፍ ሲጥላቸው እጃችው ላይ ያለው መጽሃፍ ተንሰሸራቶ ሲወድቅ ኮሚዲኖ ላይ ያለውን ሻማ ይጥለዋል፤ ሻማው መሬት ሲወድቀ መስኮቱ ስር ያለው መጋረጃን በእሳት ያያይዘዋል፤ ቤቱ በጭስ ይሞላል፤ ይህን ጊዜ ነው ፕሮፌሰር መተንፈስ አቅቷቸው ሲያስሉ ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች የደረሱላቸውና የግል ዶክተራቸውን የጠሩት፡፡

Professor Andrias Eshete

ዶክተሩ እንደመጡ ምርመራ አድርገው በአስቸኳይ ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንዲሄዱ ያደረጋሉ፤ ፕሮፌሰር ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በመተንፈሻ መሳሪያ እርዳታ አየር እንዲስቡ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ከሳምንት በላይ በዚህ ሁኔታ ሊቆዩ አልቻሉም፤ ከመተንፈሻ አላቸው መጎዳት በተጨማሪ ቀደም ሲል የነበረባቸው ተደራራቢ ቋሚ ህመም ሳቢያ እዛው ሆስፒታል ውስጥ ነሃሴ 23 ቀን 2016 ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

ከ1997 እስከ 2003 ድረስ በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉበት የአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ በመጪው ሳምንት አጋማሽ ምሁራዊ አበርክቷቸው ላይ ያተኮሩ የውይይትና የስንብት መርሃ ግብረ እያዘጋጀ ሲሆን የልጆቻቸውን ወደ ሃገር ቤት መምጣትን ተከትሎ የቀብር ስነ ስርአታቸው በሳምንቱ መጨረሻ የፊታችን እሁድ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe