10 ተጨማሪ የአውሮፓ ጋዝ ሸማቾች የሩስያን ጋዝ በሩብል ለመገበያየት ተስማሙ

10 የሚሆኑ ተጨማሪ የአውሮፓ ጋዝ ሸማቾች የሩስያን ጋዝ በሩብል ለመገበያየት ተስማምተዋል።
በዚህም ከሩሲያ ጋዝን በሩብል የሚገዙ ደንበኞች ቁጥር በጠቃላይ ወደ 20 የሚያድግ ይሆናል።
በአውሮፓ የሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች የሩስያ ጋዝ አቅራቢ ከሆነው ጋዝፕሮም ኩባንያ ጋር በሩብል ለመገበያየት ሙሉ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኝም ብሉምበርግ ዘግቧል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን ወደ 14 የሚጠጉ ድርጅቶች ፍላጎታቸውን ማቅረባቸው ተዘግቧል።
ሩሲያ ከዚህ ቀደም አሜሪካን ጨምሮ የአውሮፓ አገራት ጋዝ በሩብል እንዲገዙ ውሳኔ ማስተላለፏ የሚታወስ ነው።
የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በምእራባውያን እና በሩሲያ መካከል ያለው ውዝግብ የቀጠለ ሲሆን ጦርነቱም መቋጫ ሳያገኝ እንደቀጠለ ከአርቲ የተገኘው ዘገባ አመልክቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe