10 ቢሊየን ብር ገቢ ያስገኛል ተብሎ የተገመተ 7ሺህ ሜትሪክ ቶን ጥጥ ለቃሚ አጥቷል

ከሰላሳና አርባ ዓመት በላይ በአፋር የሚመረተውን ጥጥ ሲለቅሙ የኖሩት ደግሞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ የሚመጡ የጥጥ ለቀማ ልምድ ያዳበሩ ወጣቶች ናቸው ።ጥጡ በሚያዝያ ተዘርቶ በመስኖ አፋር ላይ ነበር የለማው ።
ወጣቶቹ እንዲህ የለቀማ ጊዜ ሲደርስ በርከት ብለው ወደ አፋር ይገቡና በካምፕ ተቀምጠው ለቀማው እሰኪጠናቀቅ ይሰነብታሉ።
ዘንድሮ እነዚህ ሙያቸው የሚፈለግ የደቡብ ወጣቶች አፋር አልሄዱም።
እሰከ መስከረም 30 ተለቅሞ መጠናቀቅ የነበረበት ብዙ የተደከመበት ጥጥ ለሁለት ቀናት በጣለ ዝናብ ከአፈር ተደባልቋል።
መንግሥት ለጥጥ ንዑስ ዘርፍ ትኩረት እሰጣለሁ ይበል እንጂ የሎጅስቲክስ ክፍተቱ አሁንም እንደሰፋ ነው።
ጥጥ እንዲያመርቱ ሲጎተጎቱ የቆዩ ባለ እርሻዎች አምነው የዘሩት ዘር ቢያፈራም በሠራተኛ እጦት ባለመለቀሙ አዝነዋል፤ ዳግም ለማልማትም እንቸገራለን እያሉ ነው።
ጥጥ ለቃሚዎቹ ለምን ዘንድሮ ቀሩ ?
”የደቡብ ኢትዮጵያ ሹሞች ሠራተኞቹን አንለቅም በማለታቸው ነው ”
ከክልሉ ለጥጥ ለቀማ አፋር የሚሄዱ ሠራተኞች በፌዴራል ፖሊስ ታጅበው ካልተንቀሳቀሱ በቀር ወደ ቦታው አንልክም ሲሉ ውሳኔያቸውን ሹሞቹ አጽንተዋል።
ፌዴራል ፖሊስ በበኩሉ የጸጥታ ስጋትም የእንቅስቃሴ ገደብም በሌለበት ሁኔታ አጃቢ ለመመደብ እቸገራለሁ ማለቱ ተሰምቷል።
የሚገርመው ጥሬ ጥጥ በማጣት ምክንያት ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ሠራተኞች እየቀነሱ ነው ።
በጥጥ ፍሬና በጥሬ ጥጥ ላይ መንግሥት አንስቶት የነበረውን VAT ዳግም መልሶታል።
***
/ከስር የሚታየው ፎቶ ግራፍ በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኝ ኩባንያ ከጥጥ ክር አምርቶ ወደ ውጭ የሚልክበት ሲሆን ጥጡ ዝነኛው የአሜሪካ ጥጥ ነው/
Via:- ሕይወት ፍሬስብሃት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe