16 የሚድያ እና የድርሰት የክብር ሽልማት አሸናፊዎች ታወቁ

አርብ ግንቦት 9/ 2016 ዓ.ም በግሮቭ ጋርደን ዎክ በተደረገው ታላቅ ሥነ- ስርአት 16 የሚድያ እና የድርሰት ሰዎች የልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።
በሽልማት መርሀ ግብሩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ታድመዋል። የሽልማቱ ሀሣብ አመንጪ እና የቃል መልቲ ሚድያ ባለቤት ደራሲ ቃል ኪዳን ሀይሉ ባደረገው ንግግር የሠራን የማመስገን ባህል ሊለመድ ይገባል ብሏል። የሽልማት ሂደቱም ሙያዊነትን እና ጥናትን መሠረት አድርጎ መካሄዱን ተናግሯል ።
በዕለቱ አዝናኝ ሙዚቃዎች የቀረቡ ሲሆን አሸናፊዎችም ዋንጫውን እንደያዙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንዳሉትም መሸለማቸው ለበለጠ ስራ እንዲነሳሱ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። ። የክብር ሽልማት ለሙያ ሥነ ምግባር ታማኝ በሆኑ የቦርድ አባላት እና አማካሪዎች የሚመራ ነው። ወደፊትም የሚቀጥል ሽልማት ሲሆን በተለይ በጥናት እና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የሽልማት ባህል እንዲሰፍን ተግቶ የሚሠራም ነው።
ዘንድሮ በሚድያ እና ድርሰት ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው።
የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ አሸናፊ
፩ኛ ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ)
የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ አሸናፊ
፫ ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ)
የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ አሸናፊ
፩ ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)
የዓመቱ ምርጥ ተውኔት አሸናፊ
፩ኛ በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ)
የዓመቱ ምርጥ ግጥምአሸናፊ
፩ኛ እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ)
የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት አሸናፊ
፩ኛ ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ)
የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ አሸናፊ
፩ኛ ችቦ (ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ)
የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥምአሸናፊ
፩ ኛላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ)
ክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን አሸናፊ
፩ኛ ኃይለመለኮት መዋዕል
የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ
፩ኛዶንኪ ቲዩብ
የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው
1ኛመንሱር አብዱልቀኒ
የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ
1ኛ አስካለ ተስፋዬ
የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት ዘመን አሸናፊ
1ኛ አማረ አረጋዊ
የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት
1ኛ ትዝታችን በኢቢኤስ
የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አሸናፊ
1ኛ ለዛ
የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ አሸናፊ
ትዕግስት በጋሻው
***

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe