2 የቢራ ፋብሪካዎች ታሸጉ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒድቴር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ባላቸው 2 የቢራ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ዛሬ አስታወቀ።

2ቱ የቢራ ፋብሪካዎች ስማቸውን አልተገለፀም።

ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ዘርግቼ እየተንቀሳቀስኩ ብገኝም አንድአንድ የማኑፍክቸሪንግ ተቋማት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ብሏል።

ይህንንም ተከትሎ በተደረገ ክትትል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ 2 የቢራ ፋብሪካዎች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ቢዝነስ ፕላን ማዘጋጀት ሲኖርባቸው የራሳቸውን የትርፍ ህዳግ ለማስፋት ሲሉ እንደፈለጉ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ተገቢነት የሌለው እና ወንጀል መሆኑ ተገልጿል።

ሁሉም የማምረቻ ተቋማት እንደዚህ ያለህገወጥ ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe