20 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከአንዲት እናት በቀዶ ጥገና ተወገደ

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከአንዲት እናት በተሳካ ቀዶ ጥገና መወገዱ ተሰማ፡፡

ታካሚዋ በሰባት ወራቸው ለእርግዝና ክትትል በመጡበት በማህፀናቸው እጢ መኖሩን ማወቃቸው የተገለፀ ሲሆን÷ የህክምና ባለሙያዎች ለፅንሱ ደህንነት ሲባል ከወሊድ በኋላ ህክምና ለመስጠት መወሰናቸው ተነግሯል።

ልጃቸውን በሰላም ከተገላገሉ በኋላም ዶክተሮች የሰጧቸውን ቀነ ቀጠሮ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ የተለየ ህመም ስለተሰማቸው በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል መጥተዋል።

ዶክተሮችም በተሳካ ሁኔታ ከሆዳቸው 20 ኪሎግራም የሚመዝን እጢ ያወጡ ሲሆን÷ አሁን ላይ ታካሚዋ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe