ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን፣ ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) የዕለት ተዕለት ስራዎቻችንን ለማቀላጠፍ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ ልህቀቶችም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ::
ከእነዚህም መካከል የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ያበለፀጋቸው በርካታ የAI መሣሪያዎች ይጠቀሳሉ:: በመሆኑም ለትክክለኛ ውጤት ትክክለኛ Ai ከመምረጥ ጋር በተያያዘ ካለው ሰፊ ችግር በመነሳት 22 ምርጥ የጎግል ሰው ሰራሽ ልህቀቶችን ላስተዋውቃችሁ:: ይህም ከፍላጎታችሁ ጋር የሚስማማውን ለመምረጥ ያስችላችኋል። (በቀጣይ ስለእያንዳንዱ Ai አጠቃቀም ተጨማሪ መረጃዎችን አጋራለሁ::)
በአጠቃላይ የጎግል የAI ስነ-ምህዳር ከግል የፈጠራ ስራዎች እስከ ግዙፍ የድርጅት ፕሮጀክቶች ድረስ ሰፊ አማራጮችን ያካትታል። አብዛኛዎቹ ለሙከራ እና ለግል አገልግሎት በነፃ የሚገኙ ቢሆንም፣ የላቁ የንግድ አገልግሎቶች እና ከፍተኛ የኮምፒውተር አቅም የሚጠይቁት ደግሞ በክፍያ የሚቀርቡ ናቸው። በነጻ የሚገኙትን በመጠቀም ስራችሁን ቀላል፣ ስኬታችሁን ፈጣን፣ ውጤታችሁን የላቀ አድርጉ።
-ያዘጋጀው ©Tesfaye T Hailu 

