26 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን የቦናፋይድ ትምህርት ቤት ህንጻ ተመረቀ

ሀዋሳ የሚገኘው ቦናፋይድ ትምህርት ቤት 26 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን ባለአራት ፎቅ ህንጻ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና የትምህርት መምሪያ ሀላፊው አቶ ደስታ ዳንኤል በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነስርአቱ ላይ የከተማው ከንቲባ፣ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ይህን መሰል ትምህርት ቤቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በቀጣይ በትምህርት ጥራት ላይ ከእዚህም ከፍ ባለ ደረጃት መስራት እንደሚገባው የገለጹት ከንቲባው ለዚህ ጥረቱም ከአስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያገኝ ተናግረዋል። ሀዋሳን የትምህርት ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ጥረት ይህን መሰል ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶች መስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን የከተማው ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳንኤል የገለጹ ሲሆን፣ የትምህርት ጥራትን የበለጠ ከፍ ለማድረግ ጠንክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ በትምህርት ጥራት ረገድ፣ ደረጃ አራት ከተሰጣቸው በጣም ጥቂት የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች አንዱ ሲሆን፣ ከቅድመ አንደኛ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡ በ2010ዓ.ም. የተመሰረተው ትምህርት ቤት 1054 ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኝ እና ሁሉን አቀፍ ጥራት በሚል መርህ በአካዳሚ ትምህርቶች እና በሥነምግባር ላይ መሰረት አድርጎ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን፣ የትምህርት ቤቱ መስራች አቶ አርጋው ጉግሳ በስነስርዓቱ ላይ ገልጸዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ ወደፊት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለመድረስ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው ተስፋ እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ አርጋው፣ እስካሁን የትምህርት መምሪያው እና የከተማ አስተዳደሩ እያደረጉ ላሉት ድጋፎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe