3 ዓለም አቀፍ የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪዎች ቦሌ ላይ በቁጥጥር ስር ዋሉ

መነሻቸውን ብራዚል ሳኦፖሎ ነው፤  መዳረሻቸው ደግሞ ዱባይና ናይጄሪያ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው አዲስ አበባ ሲደርሱ ግን የጸጥታ አስከባሪዎችን ትኩረት የሚስብ ሁኔታ ይታይባቸው ነበር ይላል ፖሊስ፤

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ሁለት ናይጄሪያዊያንና አንዲት ብራዚላዊት ናቸው፤ከብራዚል ሳኦፖሎ ተነስተው  ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ላለመፈተሸ ያንገራግሩ ነበር ተብሏል፤ ነገር ግን ህግ ህግ ነውና  በተደረገባቸው ፍተሻ አደገኛ እፅ መያዛቸው ይረጋገጣል – እጅ ከፍንጅ፤

ብራዚላዊቷ  አደገኛ ዕፁን በውስጣዊ የሻንጣ አካል በመደበቅ ለማሳለፍ ስትሞክር ናይጄሪያውያኑ ግን እፁን ከኢትዮጵያ የጉሙሩክ ሰራተኞች እይታ ውጭ ለማድረግ የሞከሩት  እፁን  ውጠው በሆዳቸው በመያዝ  ነበር፤ ያም ሆኖ ግን  የፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሶስት የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ መካከል በብራዚላዊቷ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከ13 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 666 ጥቅል ፍሬና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ከ17 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 11 እሽግ ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በሻንጣዋ ይዛ መገኘቷን ኢንስፔክተር አዲሱ ባለሚ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ናይጄሪያዊያን አደገኛ ዕፁን በሆዳቸው ይዘው ሊያዘዋውሩ እንደሚችሉ በመጠራጠር በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በተደረገላቸው የኤክስ ሬይ ምርመራ የተገኘባቸው ሲሆን 1,650 ግራም የሚመዝን 83 ፍሬ ኮኬይን ከሆዳቸው እንዲወጣ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ ሰዎችን ለወንጀል የሚያነሳሳ በመሆኑ እንዳይዘዋወር፣ እንዳይመረት እና በጥቅም ላይ እንዳይውል በህግ የተከለከለ አደገኛ ዕፅ ይዘው ሲያዘዋዉሩ በመገኘታቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe