300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመርቀ

ዴፖው ከመሬት በታች የሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያን ያካተተ ሲሆን ዴፖውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ ናቸው።

የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ዘመናዊ ጋራዥ፣ዘመናዊ ነዳጅ ማደያዎችን፣የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም መቀባት የሚችል እንዲሁም አንድን አውቶብስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ማጠብ የሚችል መሳሪያ ተገጥሞለታል።

Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…

የዴፖው መጠናቀቅ በከተማዋ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በስኬት መጠናቀቅ የጀመርነውን መጨረስ እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ የተያዙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ የሚጠናቀቁ አዳዲስ ፕሮጀክቶችም የሚጀመሩ ይሆናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ ትራንስፖርት ስርአትን ማዘመን ላይ ትኩረት አድርጓል ያሉት ኢ/ር ታከለ በተለይም በመካከከለኛና በዝቅተኛ የኑሮ እርከን ላይ የሚገኙ ዜጎችን የሚገለገሉባቸው የትራንስፖር አማራጮችን ማሳደግና ማዘመን የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ ትኩረት ናቸው ብለዋል።

Read also:ጤና ሚኒስቴር ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የቀውስ ጊዜ መረጃ አሰጣጥ ፕሮቶኮል…

አዲስ የተመረቀው የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ከወራት በፊት ከተመረቀው የሸጎሌ አውቶብስ ዴፖ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።በመርካቶ አካባቢ ተጨማሪ የአውቶብስ ዴፖ በግንባታ ላይ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe