ዓለም የሚያውቀው፣ እኛ የማናውቀው ኢትዮጵያዊ ደራሲ

በቅርብ ጊዜ ኢንተርኔቱን ስጎረጉር ነው ያወቅኩት። በድርሰቱ በዓለም ዙሪያ የተደነቀ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነው። ታዲያ በርካቶቻችን ሳናውቀው በውጪው ዓለም ከፍተኛ ዝና ማግኘቱ አስገረመኝና ለዚህ ገጽ ተከታዮች በአጭሩ ላስተዋውቀው ፈለግኩ።
ዲናው መንግሥቱ ይባላል። እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 1978 በአዲስ አበባ ከተማ ነው የተወለደው። የሁለት ዓመት ልጅ እያለ እናቱ ከቀይ ሽብር ዘመቻ ሸሽቶ ወደ አሜሪካ ከገባው ወላጅ አባቱ ጋር ልታኖረው ከኢትዮጵያ ይዛው ሄደች። ከዚያ ወዲህ የአሜሪካ ነዋሪ ነው።
ዲናው መንግሥቱ ከጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ስነ-ጽሑፍ በቢ.ኤ ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በፋይናንሺያል አድሚኒስትሬሽን የማስትሬት ዲግሪውን ተቀብሏል። በስራው ዓለምም በተለያዩ ድርጅቶች ሰርቷል።
ዲናው እስከ 2007 (እ.ኤ.አ) እንደ ማንኛውም ግለሰብ ድምጹን አጥፍቶ ስራውን ይሰራ ነበር። ከ2007 ወዲህ ግን በእንግሊዝኛ ስነ-ጽሑፍ አንባቢዎች ዘንድ እንደ ብራንድ የሚታይ ክስተት ሆኗል። ከ2008 ጀምሮ ደግሞ ታዋቂውን Wallstreet Journal ጋዜጣ ጨምሮ በበርካታ የአሜሪካ ጋዜጦችና መጽሔቶች በዓምደኝነት እየጻፈ ነው።
ዲናው በአሜሪካዊያንና በሌሎች የእንግሊዝኛ አንባቢዎች ዘንድ እንዲታወቅ ምክንያት የሆነው በ2007 ያሳተመው “The Beautiful Things that Heaven Bears” የተሰኘ የልብ ወለድ ድርሰቱ ነው። ያ ድርሰት በNewTimes ጋዜጣ እና በሌሎች ሐያሲዎች ብዕር “ከዓመቱ ምርጥ ድርሰቶች አንዱ” ተብሎ የተወደሰ ነው። ከተለያዩ ድርጅቶችም ሽልማቶችን አሽንፏል።
ዲናው ከሶስት ዓመታት በኋላ “How to Rad the Air” በሚል ርእስ ሁለተኛ መጽሐፉን ሲጽፍ ደግሞ እውቅናው የበለጠ ነው የጨመረው። ይህ መጽሐፍ በብዙ ድርጅቶች “የዓመቱ ምርጥ መጽሐፍ” ተብሎ የተሸለመ ሲሆን ታዋቂው “The New Yorker” መጽሔት ዲናው “ዕድሜአቸው ከአርባ ዓመት በታች የሆነ 20 ምርጥ የዓለማችን ደራሲዎች” በሚለው ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።
ዲናው መንግሥቱ ሶስተኛ መጽሐፉን “All Our Names” በሚል ርእስ ነበር ያሳተመው። ይህኛውም ድርሰት እንደ ቀዳሚ ድርሰቶቹ በNew York Times ጋዜጣና በሌሎች ተቋማት በጣም ተደንቆለታል። በብዙ ተቋማትም ተሸልሟል። የNew York Times ጋዜጣ የመጽሐፍ ገምጋሚዎች ስለዚህ መጽሐፍ ሲጽፉ የሚከተለውን ብለዋል።
“You can’t turn the pages fast enough, and when you’re done, your first impulse is to go back to the beginning and start over . . . While questions of race, ethnicity, and point of origin do crop up repeatedly in Mengestu’s fiction, they are merely his raw materials, the fuel with which he so artfully—but never didactically—kindles disruptive, disturbing stories exploring the puzzles of identity, place, and human connection.”
——
ዲናው መንግሥቱን ያወቅኩት ባለፈው ዓመት በGoogle ድረ-ገጽ ላይ “Best African Novelists” የሚል ሐረግ ጽፌ ኢንተርኔቱን ስጎለጉል ነው። መጀመሪያ ላይ ስሙ ከቺንዋ አቼቤ እና ከዎሌ ሶይንካ ጋር ተሰልፎ ሳየው ግራ ተጋብቼ ነበር። ስሙን በበርካታ ድረ-ገጾች ላይ ሳየው ነው የእውነት መሆኑን ያመንኩት። አንዳንድ ዌብሳይቶች ዲናውን ሲገልጹት “ከምንጊዜም ምርጥ አስር አፍሪቃዊ ደራሲዎች አንዱ ነው” ብለው ጽፈዋል (እርግጥ ድረ-ገጾቹ አንድ ስሕተት ፈጽመዋል። በዝርዝሮቹ ውስጥ ያካተቷቸው ደራሲዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ የሚጽፉ ናቸው። በሌሎች ቋንቋዎች የሚጽፉ እውቅ አፍሪቃዊ ደራሲዎች በዝርዝሮቹ ላይ አልተጠቀሱም)።
—–
ከላይ እንደገለጽኩት ዲናው መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት ለተለያዩ መጽሔቶችና ጋዜጦች ይጽፋል። በመደበኛ ስራው ደግሞ በኒውዮርክ ከተማ እምብት የሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የጽሑፍ ጥበብ (Written Art) የፕሮግራም ዲሬክተር ሆኖ ያገለግላል።
Dinaw Mengestu was born in Addis Ababa, Ethiopia, in 1978. He is the recipient of a fellowship in fiction from the New York Foundation for the Arts and a Lannan Literary Award, and received a “”5 under 35″” Award from the National Book Foundation.
His first novel, The Beautiful Things That Heaven Bears, was named a New York Times Notable Book and awarded the Guardian First Book Award and the Los Angeles Times Art Seidenbaum Award for First Fiction, among numerous other honors.
He lives with his wife and son in Paris.
——-
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe