” የንጹሓን ደም በከንቱ መፍሰስን ማስቆም የሚችለው ሕሊና ያለው ሕዝብና ፈጣሪ ብቻ ነው ” – እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፤ ከሰሞኑ በምሥራቅ ወለጋ በጊዳአያና፣ ኪረሙና ሐሮ ቀበሌዎች በየቀኑ በሚባል ደረጃ የሰው ህይወት እያለፈ እንደሆነ አሳውቋል።

” የየቀኑ የሚፈሰው ደም የኢትዮጵያ ምድር ይህን ያህል ደም ተጠምቷልን ? ያሰኛል ” ያለው ፓርቲው ” እሥረኞች ተገድለዋል፣ ንጹሓን በእምነት ቦታዎች ጭምር ተጨፍጭፈዋል፣ ብዙ ሺዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ” ብሏል።

በመሆኑም፦

– መንግስት ለአካባቢው ልዩ ትኩርት በማድረግና በቂ የመከላከያ ኃይል በማሰማራት የንጹሓንን እልቂት በአፋጣኝ እንዲያስቆምና የአካባቢው ዘላቂ ሰላም እስከሚረጋገጥ ድረስ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር በአጽንዖት እናሳስቧል።

– ግጭቱ ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀየረ የእርስ በእርስ ወደመሆን ከመሄዱ በፊት ያገባኛል የሚሉ አካላት በሙሉ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

– እልቂቱን በዘላቂነት ለመፍታት ከአድሏዊነት በጸዳ መልኩ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማወያየትና ችግሩን በጥልቀት በመረዳት የመፍትሔ ሀሳብ እንዲፈለግም ጠይቋል።

ፓርቲው፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ የንጹሓንን መታረድ ዝም ብሎ ማየት ኃጢያትም ወንጀልም ነው ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ኹሉ የእነዚህን በየቀኑ የሚታረዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ለመታደግ በሕሊናም በፈጣሪም ፊት ከተጠያቂነት ለመዳን በመወያየትና መፍትሔ እንዲፈልጉ፤ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስትና በፌዴራል መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ፤ ድርጊቱንም እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርቧል።

” የንጹሓን ደም በከንቱ መፍሰስን ማስቆም የሚችለው ሕሊና ያለው ሕዝብና ፈጣሪ ብቻ ነው ” ያለው እናት ፓርቲ “ይህን ተረድተን ኹላችንም የምንችለውን እንድናደርግ” ብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe