45 ከመቶ መራጮች የመረጃ ምንጫቸው ቴሌቪዥን መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ * ማህበራዊ ሚዲያው 18 ከመቶ ይዟል፡፡

ስለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ የተጠየቁ መራጮች በመጪው የ6ኛ ብሄራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኞች ሲሆኑ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ግን እንደሚያሳስባቸው ጨምረው ተናግረዋል።

ጥናቱን ያካሄደው ኢትዮፖል ኮንሰልት እንዳመለከተው “ከአስር ዘጠኝ እጅ የሚሆኑ (89%) በስልክ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ላይ ተሳታፊ የሆኑ መራጮች በመጪው ብሔራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጁነን ብለዋል። በምርጫው የመሳተፍ

ፈቃደኝነት እንደየመራጩ እድሜ ይለያያል። ከ62 አመት በላይ መራጮች በከፍተኛ ቁጥር ፈቃደኝነታቸውን ሲገልጹ በአንጻሩ ሶስት አራተኛ የሚሆኑት ወጣት መራጮች (18-23 አመት) በምርጫው ለመሳተፍ ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል። ለምርጫ ውሳኔዎ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ 98% የሚሆኑ መራጮች የሰላምና ደህንነት ሁኔታ “በጣም ወሳኝ” ነው ብለዋል።

ዳሰሳው የተለያዩ ጉዳዮችን የሸፈነ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የመራጮችን በምርጫው ለመሳተፍ ያላቸውን እቅድ፣ ዋና ዋና የሚሉዋቸውን የፖሊሲ ጉዳዮች ፣ ምርጫውን በተመለከተ የሚጠቀሙዋቸውን የመረጃ ምንጮች፣ ስለምርጫው አሰራር

ያላቸውን የግል ግንዛቤና ግምት እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ምን እንደሚጠብቁ የሚሉ ጉዳዮችን ይገኙባቸዋል።

መራጮች ለመምረጥ የሚያስችላቸውን መረጃ ከየት እንደሚያገኙ የተጠየቁ የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት 45 ከመቶ ያሉ ቴሌቪዥን ሲያስቀድሙ 26 ከመቶ የሚሆኑ መላሾች ራዲዮን ቀዳሚ የመረጃ ምንጫቸው አድርገዋል፡፡ 18 ከመቶ ያህሉ መላሾች ማህበራዊ ሚዲያውን እንደቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ሲጠቀሙ ዘመድ አዝማድን የመረጃ ምንጭ አድርገው ወደ ምርጫ ጣቢያ የሚሄዱ ሰዎች 6 ከመቶ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ስለ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ በቂ መረጃ አለን ያሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች 57 ከመቶ ብቻ ያህል ሲሆኑ መረጃ የሌላቸው መራጮች 43 ከመቶ  ናቸው፡፡ ይህም የመራጮች ትምህርት አስፈላጊነቱን አሳይቷል፡፡

ኢትዮፖል ይህን አገር አቀፍ የሆነ የተንቅሳቃሽ ስልክ የዳሰሳ ጥናት ያደረገው በእስታትስቲክስ ቀመር ውክልና ሊሰጡ በሚያስችሉ 856 ግለሰቦች ሲሆን እድሜያቸው ከ 18 አመት እና ከዛ በላይ በሆኑ ዜጎች ተሳትፎ ነው። ጥናቱ የተካሄደው ከመጋቢት 20 2013 እስከ ሚያዚያ 5 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ነበር። የጥናቱ አስተባባሪዎች እንዳሳሰቡት የተንቀሳቃሽ ስልክ በኢትዮጲያ ውስጥ

ስርጭቱ በጣም ውስን፣ተጠቃሚዎቹም በአብዛኛው ወጣት፣ ከተሜ እና ወንዶች ናቸው። ስለዚህ የዚህን ጥናት ውጤት እንደ የአጠቃላይ የአገሪቱ መራጭ አስተያየት ከማድረግ በፊት እነዚህ የተጠቀሱትን የጥናቱን ውስንነቶች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት

ያስፈልጋል። በአንጻሩ የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥናት ተመራጭ ከሆነባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው መረጃን በፍጥነት መሰብሰብ ማስቻሉ ነው። በኢትዮጲያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው የስልክ አገልግሎት ሽፋን የተንቀሳቃሽ

ስልክ ዳሰሳን ተመራጭነት ያሳድገዋል።

የጥናቱ ሙሉ ሪፖርት አርብ ሚያዚያ 15 2013 ከሰአት 8 ሰአት ላይ በተደረገ የዙም ስብሰባ ላይ ይፋ ሆኗል።

የኢትዮፖል ባለሙያዎች በጥናቱ ላይ ማብራሪያ እና ምላሽ እንደዚሁም የወደፊት የስራ እቅዳቸውን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe