49 ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት ተነጠቁ

በደቡብ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ማልማት ያልጀመሩ 49 ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት እንደተነጠቁ ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት ወስደው ምንም ዓይነት የልማት ሥራ ባልጀመሩ 49 ባለሀብቶች ላይ የመሬት መንጠቅ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወይዘሮ አፀደ አይዛ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ በክልሉ ለማልማት መሬት ወስደው ግዴታቸውን ባልተወጡ በአጠቃላይ 81 ባለሀብቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

በዚህም መሠረት 49 ባለሀብቶች የወሰዱት መሬት እንዲነጠቅ የተደረገ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 32 ባለሀብቶች ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

እንደ ኮሚሽነሯ ገለጻ፣ በእርምጃው የተነጠቀው 13 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ተደርጓል።

ይህ የተመለሰ መሬት በክልሉ ለሚያለሙ ሌሎች ባለሀብቶች እንደሚተላለፍም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ 1ሺህ 800 ባለሀብቶች በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 226 አዳዲስ ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን ወይዘሮ አፀደ አብራርተዋል።

ኮሚሽነሯ ባለሀብቶች ክልሉ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
መሬታቸው የተነጠቀባቸው ባለሀብቶች በወሰዱት መሬት ላይ ሥራ ያልጀመሩበት ምክንያት አልተጠቀሰም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe