አበረታች መድኃኒቶች ምንድናቸው?

ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባሳለፈው የአንድ መቶ ዓመት ጊዜ በርካታ ፈተናዎች አጋጥመውታል፡፡ በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሳቢያ የኦሎምፒክ ውድድሮች ሲስተጓጎሉ፣ በምስራቅና በምዕራብ ዓለም የአይዲዎሎጂ ልዩነት ሳቢያም አገራት ራሳቸውን ከውድድሩ በማግለላቸው ዓለማቀፋዊነቱ ደብዝዞ ቆይቷል፡፡ ይሄ ሁሉ ካለፈ በኋላ ደግሞ የኦሎምፒክና መሰል ታላላቅ ወድድሮችን የሚፈታተን ነገር ተከሰተ አበረታችን መድሃኒቶች፡ ፡ ከኦሎምፒክ ውድድሮች እስከ ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች አበረታች መድሃኒቶች የውድድሩ አዘጋጆች የሥጋት ምንጭ ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ባለው የስፖርተ ውድድሮች ላይም ተመሳሳይ ሁኔታዎች እየታየ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ከ1990ዎች አጋማሽ ጀምሮ የጣሊያን ህዝብን በእግር ኳስ የአጨዋወት ችሎታው ያሳበደው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ድፍን የናፖሊ ከተማን ህዝብ በደስታ ማስጨፈሩ አይዘነጋም፡፡ ቀኝ እጁን ወደታች ግራ እጅኑ ወደፊት ሰድሮ በግራ እገሩ ኳሷን እንዳሻው በማዘዝ ለጣሊያን ካቴና ተከላካዮች ራስ ምታት የነበረው ማራዶና ዋጫ ለመሳም ቀርቶ በቅርብ ርቀት አይቶ የማያውቀውን የናፖሊን ክለብ ደጋፊ የሴሪኣው የበላይ በማድረግ ዋንጫ እንዲስም አደርጓል፡፡ የክለቡን ብቻ ሳይሆን መላ የጣሊያንን የእግር ኳስ አፍቃሪ በሰንበት ቀን እንኳ እግዚአብሔርን እንዳስረሳ የሚነገርለት ማራዶና የኋላ የኋላ ታሪኩ በአበረታች መድኃኒት ሳቢያ ሳያምርበት ነው ከእግር ኳስ ዓለም ተሰናብቶ ክዚህ አለም የተለየው፡፡

ለማራዶና የቅሌት ማቅ መልበስ ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተከሰተው ምን እንኳን ቀደም ሲል ቢሆንም ይፋ ወጥቶ የሀፍረት ካባን የተከናነበው ግን እ.ኤ.አ በ1994 አሜሪካ ባዘጋጀችው አስራ አምስተኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ነው፡፡ በስፔን የክለቦች ጨዋታ ላይ ኢፊዲሪን የተባለ አበረታች መድኃኒት ወስዶ በመገኘቱ ከጨዋታ የታገደው ማራዶና ‹መድኃኒቱን ለአስም ህመሜ ማስታገሻ ነው› የወስድኩት ይበል እንጂ የምርመራ ውጤቱ ያመለከተው ተገላቢጦሹን ነው፡፡

ለ18 ወራት ያህል ከውድድር ታግዶ የቆየው ማራዶና የቀድሞ ስሙን ለማደስና ዳግሞ ሀገሩን ለዓለም ዋንጫ ድል ለማብቃት ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ ወደ አሜሪካ ተጉዞ ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ጨዋታ ሀገሩ አርጀንቲና ከግሪክ ጋር ባደረገችበት ወቅት የቡድኑ እንቀሳቃሽ ሞት የነበረው ማራዶና ከእረፍት መልስ ከ20 ሜትር ርቀት ላይ በተአምረኛ ግራ እግሩ የላካትን ኳስ የግሪኩ በረኛ ለማዳን ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም ነበር፡፡ ለሀገሩ ድል ያስመዘገበው ማራዶና ከጨዋታው በኋላ በራስ የመተማመን ስሜት ቢነበብበትም የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራር አባላት ግን የማራዶና ሜዳ ሙሉ ሩጫ ላይ ጥርጣሬ ነበራቸው፡፡

ጨዋታው እንደተጠናቀቀ እንደማንኛውም ተጨዋች ማልያውን አውልቆ ደስታውን ይገልፅ ወደ ነበረው ወደ ማራዶና ያመሩት የፊፋ የህክምና ክፍል ኃላፊ በቀጥታ የማራዶናን እጅ እንደ ህፃን ልጅ ይዘው የገቡት በስታዲየሙ ምድር ቤት ወደ አለው የህክምና ማዕከል ነበር፡፡ ማራዶና በሁኔታው ቢደናገጥም ምርመራ አላደረግም ለማለት ግን አልደፈረም፡፡ የምርመራው ውጤት ሲገለፅ የፊፋ ባለስልጣናት ጥርጣሬ እውነት ሆነ፡፡ ማራዶና ወደ ጨዋታው ከመግባቱ በፊቱ አበረታች መድኃኒኒ መውሰዱ ይፋ ሆነ፡፡ ብዙዎች በምተሃታዊ እግሩ በሚሰራው አብዶ ያስደስት የነበረው የኳስ ጀግና ዳግመኛ በስሙ በክብሩና በማንነቱ ላይ ጥቁር ነጥብ ወደቀ፡፡ ማራዶና ምንም እንኳን ‹‹የወሰድኩት መድኃኒት የለም የእኔን መጥፎ የሚያስቡ ሀኪሞች ናቸው::

ቢከራከርም የቀድሞ ስሙን እንደያዘ ከስፖርት አደባባይ መገለል አልቻለም፡፡ የአበረታች መድኃኒቶች መስፋፋትና በስፖርተኞች ዘንድ መዘውተር የፊፋ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ አማተር አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የዓለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ ራስ ምታት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ስፖርት ነፃ ሆነው የውድድር መንፈስ ውጪ የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶች እየወሰዱ ለውድድር በመግባት የስፖርቱን ገፅታ በሚያበላሹ ስፖርተኞች ላይ የአመራር አባላቱ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተገደዋል፡፡

በመጀመሪያ ሀይል ይሰጣሉ፤ ያበረታታሉ የተባሉ መድኃኒቶችን ስፖርተኛች መጠቀም እንደሌለባቸው የመድኃኒቶችን ዝርዝር ይፋ በማድረግ ሥራ የተጠመዱት የፊፋና የአለምአቀፍ አማተር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መድኃኒቱን ወስዶ ወደ ውድደር የገባ ስፖርተኛ ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጥሉ አስታውቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተቋማቱ የመድኃኒቶችን ዝርዝር ያውጡ እንጂ አንድ ስፖርተኛ አበረታች መድኃኒት መጠቀም ያለመጠቀሙን ለማወቅ የሚያስችለው ምርምራ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አስተማማኝ አልበረም፡፡

ስፖተኞች ውድድር አደርገው እንደጨረሱ የሽንት ምርመራ እንደዲደረግላቸው የሚደነግገው የባለ ሥልጣናቱ መመሪያ በስፖርተኞች ቀላል ዘዴ በተደጋጋሚ ተጭበርብሯል፡፡ ምርመራውን የሚያደርጉት ሀኪሞች ስፖርተኞች ሽንታቸውን እንዲሰጡ በሚጠይቋቸው ጊዜ ወደ መፀዳጃ ቤት ገብተው አስቀድሞ የገባውን የጓደኛቸውን ሽንት በብልቃጥ ይዘው በመምጣት ነበር የሚያስመረምሩት፡፡ ይህ ዘዴ ሲነቃባቸው ደግሞ ቀደም ሲል ከሀገራቸው ሲነሱ በብልቃጥ ሽንታቸውን በመያዝ በሻንጣቸው አደርገው ብልቃጡን በመቀየር ያስረክቡ ጀመር፡፡ እነዚህ ተራ የማጭበርበር ተግባራት በየመፀዳጃ ቤቱ ጣራ ላይ በሚሰቀሉትና ሲሸኑ በሚቀርፀው ካሜራ አማካኝነት እልባት ቢገኝም አሁንም ቢሆን የሽንት ምርመራው መቶ በመቶ አስተማማኝ አላደረገውም፡፡ በመሆኑም ፊፋና አለም አቀፍ አማተር አትሌቲክ ፌዴሬሽን ስፖርተኞ እዛው ሀኪሞች ፊት እንዲሸኑ በመጠየቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ ስፖርተኞች ካሉ ደግሞ የደም ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚደነግግ መመሪያ አውጥተዋል፡፡

አንድ ስፖርተኛ ሽንቱ ተመርምሮ አጠራጣሪ ሁኔታ ካጋጠመ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በሀኪሞች ውሳኔ የደም ምርመራ ማድረግ የግድ ከሆነ ደም እንዲሰጥ በማድረግ አበረታች መድኃኒት መውሰድ ያለመውሰዱ ይረጋገጥበታል፡፡ እያንዳንዱ የስፖርት አይነት በበላይነት የሚመራው ፌዴሬሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላለ ስፖርተኞ ከአበረታች መድኃኒት ነፃ መሆናቸውን ወደ ውድድር ሲገቡም ሆነ ሲወጡ እንዲያረጋግጡ ግዴተጥሎባቸዋል፡፡

የኦሎምፒክ ስፖርቶችን በተመለከተ የማንናኛም ሀገር የስፖርት አመራር ይዞት የሚመጣው ስፖርተኛ ከእንዲዚህ አይነት አፀያፊ ተግባር ነፃ መሆኑን ማረጋግጥ ያለበት ሲሆን በእንግሊዝ ይህንን ኃላፊነት የሚወስድ የስፖርት ካውንስል አለ፡፡

አበረታች የተባሉ መድኃኒቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ የሚዋጡ፣ የሚጠጡ፣የሚመጠጡና የሚቀቡ ተብለው ይከፈላሉ፡፡ የአለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኦሎሚፒክ ኮሚቴ በስፖርተኞች አዘውትረው የሚወሰዱ ያሏቸውን የተወሰኑ አበረታች መድኃኒቶች በየጊዜው ይፋ ያደርጋሉ፡፡ ከእነዚህም መሀከል /Stimulants, narcotic analgesics, anabolic agents and diuretics / ይጠቀሳሉ፡ ፡ እዚህ መድኃኒቶች ሲወሰዱ በስፖርተኞ ላይ የተለያዩ ለውጦች የሚያስከትሉ ሲሆን በጤናቸው ላይም ጉዳት ያደርሳሉ፡፡

አነቃቂዎች /Stimulants /

አምፊትሪሚን /Amphetamines/ እና ኮኬይን አነቃቂ ተብለው ከሚጠቀሱት አበረታች መድኃኒቶች መሀከል ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ መድኃኒቶቹ አንድ ስፖርተኛ በውድድር ወቅት ንቁና ተፎካካሪ ሆኖ እንዲቀርብ ያስችለዋል፡፡ መድኃኒቱን የወሰደ ስፖርተኛ በውድድር ወቅት የድካም ስሜት አይሰማውም፡፡ መድኃኒቱ በቀዳሚነት የልብ ምትን ፍጥነት የሚጨምር ሲሆን የደም ግፊት እንዳያይል ያደርጋል፡፡ መድኃኒቱ ለጊዜው ህመም እንዳይኖር ይደብቃል፡፡ ቆይቶ ግን ንቀትና ንዴት ያስከትላል፡፡

አነቃቂ ተብለው የሚታወቁት በአብዛኛው በፋብሪካ የሚቀመሙ መድኃኒቶች ቢሆኑም በተፈጥሮ የሚገኙ አነቃቂዎችም አሉ፡፡ ከእዚም ውስጥ ካፌን የተባው ንጥረ ነገር የሚይዙት ቡናና ሻይ በአነቃቂነት የሚታወቁ ቢሆንም የካፌን መጠናቸው ከፍተኛ ባለመሆኑ ለስፖርተኞ የተከለከሉ አይደሉም፡፡ ሲጋራ ግን ለስፖርተኞ የተፈቀደ አይደለም፡፡

የሱስ ማስታገሻመድኃኒቶች /Narcotic Analgesics/

በሱስ የተጠመዱ ሰዎች ሱሳቸውን ለማስታሻ ከሚጠቀሙበት መድኃኒች መሃከል ሜታዶን፣ ሄሮይንና ኮኬይን ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ አበረታች እፆች በሚወሰዱ ጊዜ ህመም የማስታገስና ጉዳት እንዳይሰማ ያደርጋሉ፡፡ መድኃኒቱን ስፖርተኞች የሚጠቀሙበት ጊዜ ደግሞ ከደረሰባቸው ጉዳት ለጊዜው የዳኑ ቢመስላቸውም ቁስሉ ቋሚና ዘላቂ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ስፖርተኛው ከህመሙ ለመሸሽ ሲል ለረጅም ጊዜ የእነዚህ ዕፆች ተጠቃሚ ለመሆን ይገደዳል፡፡ ኮኬይን ለመድኃኒት መቀመሚያ የሚውል እፅ ቢሆንም ያለሀኪም ትዕዛዝ መውሰድ

አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡

አካል መገንቢያ ዕፆች /Anabolic Agents/

የሰውነት አካላት ከተለመደው መንገድ ውጪ ለማፋትና ለመገንባት እገዛ ከሚያደርጉት አበረታች መድኃኒቶች መሀከል ቴስትሮን፣ ስታኖዞላ ከሌንቡተሮል ይጠቀሳሉ፡፡ መድኃኒቶቹ በሚወደዱበት ጊዜ ለስፖተኛው ጥንካሬ የክብደት መጨመርና በውድድር ላይ ፅናት እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡

እነዚህ ዕፆች በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚያሳዩት ምልክት የተለያየ ነው፡፡ ወንዶች በሚወስዱበት ጊዜ ጠብ አጫሪ ያደርጋቸዋል፡፡ ስንፈተ ወሲብ ከማስከተሉም በላይ ለኩላሊት ህመም ይዳረጋሉ፡፡ የፀጉር መሳሳት መመለጥ ብሎም ራስ በራነት ወሎ ሳያደር የሚከሰትችግር ሲሆን ከተለመደው ውጪ አንደ ሴቶች ጡቱ ሊያድግ ይችላል፡፡ በሴቶች ላይ ደግሞ ወንዳ ወንድ ባህሪን የሚያላብስ ሲሆን በወንድ አካል ላይ የሚታዩ ለውጦች ማለትም ፂም ማብቀል ጡንቻ ማውጣትና የድምፅ መጎርነን ይከሰታል፡፡ ከዚህ ሌላ ወቅቱን ያልጠበቀ የወር አበባ መፍሰሰም ያጋጥማል፡፡

ለመሆኑ የስፖርተኞች ምርመራ እንዴት ይከናወናል?

በኢንተርናሽና አማተር አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ሆነ በአለም አቀፍ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ህግ መሠረት ማንኛውም ስፖርተኛ ወደ ውድድር ከመግባቱ በፊም ሆነ በኋላ እንደአስፈላጊነቱ ምርመራ ሊደረግበት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ምርመራው የሚደረገው ለሁሉም ተወዳዳሪዎች ወይም ለተወሰኑ ስፖርተኞች ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

ሐኪሞቹ ማን መመርመር እንዳለበት አስቀድመው በመወሰን ለስፖርት ኃላፊዎች የተወዳደሪውን ስም በፅሑፍ ያሳውቃሉ፡፡ የተወዳዳሪው ስም የደረሳቸው የስፖርቱ አመራር አባላት ስፖርተኛውን ይዘው ወደ ምርመራ ማዕከሉ ያመራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ስለስፖርተኛው የጤና አቋም የሚገልፁ ዶክሜንቶች የስፖርተኛው ሀኪሞች እንዲቀርቡ ያደርጋሉ፡፡

ስፖርተኛው እየወሰዳቸው ያሉ መድኃኒቶች ወይም አስቀድሞ የወሰደው የመድኃኒት አይነት ሀኪሞቹ እንዲገልፁ ይጠየቃሉ፡፡ ምርመራው ከስፖርተኛው ሽንት ይጀምራል፡፡ የስፖርተኛው ሽንት በሁለት ብልቃጥ ተከፍሎ የትኛው ብልቃጥ እንዲመረመር እንደሚፈልጉ እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡ ቀሪው ያልተመረጠው የስፖርተኛውን ሽንት የያዘው ብልቃጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የሽንት ማቆያ ፍሪጅ ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡

ምርመራው በላብራቶሪ ከተከናወነ በኋላ ስፖርተኛው እፅ መውሰዱን የሚያመለክት ነገር ከሌለ በፍሪጅ ውስጥ የተቀመጠው ሁለተኛው የሽንት ብልቃጥ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ ከዚያም ውጤቱ ለስፖርት አመራሮችና ለስፖርተኛው ይገለፅለታል፡፡

የምርመራ ውጤቱ ፖዚቲቭ ከሆነ ማለትም በሽንቱ ውስጥ እፅ መውሰዱን የሚያመለክት ነገር ከተገኘ ስፖርተኛው ይታገዳል፡፡ በፍሪጅ ውስጥ ከተቀመጠው ሁለተኛው የሽንት ብልቃጥ ላይ ድጋሚ ምርመራ እንዲደረግ ስፖርተኛው ከጠየቀ ምርመራ ይደረጋል፡፡

ሁለተኛው ምርመራ ውጤት አሁንም ፖዘቲቭ ከሆነ ለስፖርት አመራሮች ውጤቱ ይገለፅና ስፖርተኛው የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ከማንኛውም ውድድር ይታገዳል፡፡ ስፖርተኛውም ሆነ የስፖርት አመራሮች በውጤቱ ላይ እምነት ከሌላቸው የደም ምርመራ እንዲደረግ የመጠየቁ መብት ያላቸው ሲሆን የደም ምርመራው ግን ከውድድሩ በኋላ ከሚከናወን ነው የሚሆነው፡፡

የስፖርተኞች ላይ የሚካሄደው ምርመራ የሚከናወነው ወደ ውድድር ሲገቡ ብቻ ሳይሆን ከጨዋታው በኋላም ሊሆን ይችላል፡፡ አበረታች መድኃኒቶችን ተጠቅመው ወደ ውድድር ከገቡ በኋላ በምርምራ የተረጋገጠባቸው ስፖርተኞች በውድድሩ ላይ ስገኙ ውጤት ካለ እንዲሰረዝ የሚደረግ ሲሆን ዳግመኛ እንዳይወዳደሩ የሚያደርግ እገዳም ሊጣልባቸው ይችላል፡፡

ከአትሌቶቻችን ጀርባ ሆነው አበረታች ቅመሞችን እንዲጠቀሙ የሚያደርጉ የሀገር ውስጥም ይሁን የውጭ ሃገር አሰልጣኞችንና ማናጀሮችን ተከታትሎና መርምሮ እርምጃ ከወዲሁ ካልተወሰደ በአበረታች ቅመሞች ስሟ ተነስቶ የማያውቀው ሃገራችን ከኦሎምፒክ መንደር እስከመታገድ የሚያደርስ ችግር ላይ ልትወድቅ ስለምትችል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የዲሪቲክ አበረታች እፆች

በተደጋጋሚ የሽንት መፍሰስን ከሚያስከትሉት የዲሪቲክ መድኃኒቶች ውስጥ ፍሩሰሚድና ፕሮቤንሲድ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እነዚህ እፆች በስፖተኞች ሲወሰዱ የሰውነት ክብደት በፍጥነት ይቀንሳል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ እፁ በየተወሰነ ሰዓቱ ሽንት እንዲመጣና በሰውነት ውስጥ ያለው ቅባትና ስብ እየሟሟ እንዲወጣ ስለሚደርግ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ይህንን እፅ የሚወስዱ ስፖርተኞች ለከፋ ራስ ምታት፤ ድርቀት፣ለጡንቻ መሸማቀቅ፣ለአእምሮ መታወክና የማጥወልወል ስሜት ይዳርጋሉ፡፡

ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ እነዚህን አበረታች መድኃኒቶች ማንኛውም ስፖርተኛ በማንኛውም ምክንያት ወስዶ ወደ ስፖርት እንዳይገባ ደንግጓል፡፡ ኮሚቴው ለዚህ ውሳኔው መነሻ የሆነው ሦስት ምክንያቶች ሲሆኑ እነሱም፤

– በአበረታች እፅ ተጠቅሞ ማሸነፍ የስፖርት ቤተሰቡን ማታለል በመሆኑ፣

– ስፖተኞች በማንኛውም መልኩ ጤነኞች ሆነው ለውድድር እንዲቀርቡ ለማድረግና፣

– የስፖርትን ነፃ የውድድር መንፈስ ለማጎልበት ነው፡፡

በርካታ ስፖርተኞች ያልተፈቀዱመድኃኒቶችን እየተጠቀሙ ወደ ውድድር ሜዳ በመግባት ለእገዳ ተዳርገዋል፡

፡ ከእነዚህም ውስጥ ከአርጅቲናው የኳስ ንጉስ ዲያጎ ማራዶና ሌላ ካናዳዊው የ100 ከውድድር ለመታገድ በቅቷል፡፡ ስፖርተኞች አበረታች መድኃኒት ወስደው ወደ ሜዳ ስለሚገቡበት መንስኤ ያጠኑት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እንዳሉት ተወዳዳሪዎች አበረታች እፅ የሚወስዱበትን የተለያዩ ምክንጣቶች ዘርዝረዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፣

– በማንኛውም መንገድ በተሰለፉበት የስፖርት አይነት የበላይ ሆኖ ለመገኘት መፈለግ፤

– መድሃኒት ወስዶ ውድድር በማሸነፍ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት መፈለግ፤

ህዝቡና ሚዲያው እንዲያሸንፉ በመፈለግ በሚያሳድሩባቸው ግፊት በመጨነቅ፣

– ማንኛውም ስፖርተኞች እነዚህን አበረታች እፆች ተጠቅሞ ነው የሚገባው የሚል የተሳሳተ አቋም በመያዝ፣

– አሰልጣኞቸው ስለሚመክሯቸው፣

– በውድድር ወቅት ከመሰለፍ ሊያስቀራቸው ከሚያስችል አንደ ጉንፋን አይነት ካሉ ህመሞች ነፃ ለመሆን ከመፈለግና እፁን ወስዶ በመወዳደር አጭበርብሮ ማሸነፍን እንደ ድል ከመቁጠር የሚመጣ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe