65 በመቶ የሚሆኑ ኬንያውያን በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደር ወቅት ድህነት እንደተባባሰባቸውና የኢኮኖሚ ሁኔታቸው እንደወረደ መግለጻቸውን አዲሱ የቲፋ (TIFA) ጥናት ይፋ አደረገ።
ጥናቱ እንደሚያሳየው፦
65% የሚሆኑት ከ2022 ምርጫ ወዲህ የቤተሰባቸው ገቢና ኑሮ እንደቀነሰ ተናግረዋል።
23% የሚሆኑት ኑሯቸው እንዳለ እንደቀጠለና ምንም እንዳልተቀየረ ገልጸዋል።
12% ብቻ ኑሯቸው እንደተሻሻለ ተናግረዋል።
በተጨማሪም 65 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ «በጣም መጥፎ» ብለውታል። በተለይም በማውንት ኬንያ (79%) እና በምዕራብ ኬንያ (74%) የሚኖሩ ሰዎች በኢኮኖሚው ላይ ያላቸው ቅሬታ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
65% ኬንያውያን በፕሬዚዳንት ሩቶ ዘመን ድህነት እንደተባባሰባቸው ገለጹ
SourceAddis maleda

