እስራኤል ለ40 ቀናት ያህል ባደረገችው ጦርነት ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋለች ተባለ

እስራኤል ከኢራን እና ከሊባኖስ ጋር ለ40 ቀናት ያህል ባደረገችው ጦርነት ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋለች ተባለ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቴላቪቭ ውስጥ ከ1ሺ በላይ መኖሪያ ቤቶች ከመኖሪያነት ወጪ እንዲሆኑ እንዳስገደደም ተዘግቧል፡፡

የእስራኤሉ ቻናል 12 በዋና ከተማዋ በኢራን የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ምክንያት ከ1ሺ በላይ አፓትራማዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ የካቲት 21 በተጀመረው የአሜሪካ፡እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ምክንያት በሁሉም ወገኖች ቀላል የማይባል ጥፋት ደርሷል፡፡ በርግጥ በዚህ ጦርነት በኢራን ላይ የደረሰው ጉዳት በሰው ሃይልም ይሁን በገንዘብ ከፍተኛ ቢሆንም በእስራኤልም ላይ ግን ቀላል የማይባል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡

የእስራኤል ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት ባወጡት ሪፖርት ሀገሪቱ ከኢራን እና ከሊባኖስ ጋር ባደረገችው የ40 ቀናት ጦርነት ውስጥ ብቻ ወደ 17.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ አድርጋለች ብለዋል፡፡

ይህ አህዛዊ መረጃ ለመልሶ ግንባታ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት በተዘጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች ምክንያት የታጣውን ገንዘብ አይጨምርም ተብሏል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች፡፡

የእስራኤል ጦር የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች ተለይተው ከተቀመጡ የአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል መስመሮች እንዳያልፉ እና ሊታኒ ወንዝ አቅራቢያ ወደሆኑ ስፍራዎች እንዳይጠጉ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

እስራኤል እና ሊባኖስ የተስማሙበት የ10 ቀናት ተኩስ አቁም ካለፈው ሳምንት አንስቶ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ ይህ ስምምነት ቢደረግም የእስራኤል ጦር ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በሚታየው የሄዝቦላህ እንቅስቃሴ ምክንያት አካባቢውን ለቅቆ እንደማይወጣ አስታውቋል፡፡

አሁን ደግሞ ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ መንደሮችን ዘርዝሮ ነዋሪዎች ወደ እነዚህ አካባቢዎች እንዳይመለሱ አስጠንቅቋል፡፡

ጦሩ የእስራኤል ነዋሪዎችን በሄዝቦላህ ከሚተኩሳቸው ሮኬቶች ለመጠበቅ ሲል ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ የደህንነት ዞን ማቋቋሙንም አስታውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም የእስራኤል ጦር ከተቆጣጠራቸው የሊባኖስ ስፍራዎች ለቅቆ እንደማይወጣ፡ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እንደማይፈቅድ እና መንደሮችን እንደሚያወድም መግለጹ ይታወሳል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe