“91 በመቶው የትግራይ ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊ ነው”- የዓለም ምግብ ፕሮግራም

የተጀመረውን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ አጠናክሮ ለማስቀጠል 203 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛልም ነው ፕሮግራሙ ያለው፡፡

ፕሮግራሙ ከአንድ ሚሊዬን ለሚልቁ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ካለው የሕዝብ ቁጥር ከ90 በመቶ በላዩ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ።

ድርጅቱ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ምላሽ የ203 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋልም ብሏል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ምዕራብ እና በደቡባዊ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመጋቢት ወር ጀምሮ ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቁ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቋል።

ከሚያዚያ ወር ተደራሽ በሆነባቸው የሰሜን ምዕራብ ዞን 13ቱም ወረዳዎች ለ885 ሺ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ችሏል፡፡

ከወርሃ መጋቢት ወዲህ ባሉት ጊዜያት ደግሞ በሶስት የደቡባዊ ዞን ወረዳዎች 168 ሺ ሰዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህም አጠቃላይ በፕሮግራሙ በኩል የተደረገውን የድጋፍ መጠን 1.05 ሚሊዬን የሚያደርስ ነው፡፡

ፕሮግራሙ በሰሜን ምዕራብ እና በደቡባዊ የክልሉ አካባቢዎች ከመሰማራቱ በፊት በምስራቃዊ ዞን 33 ሺ ሰዎችን ለመደገፍ ችሏል፡፡

ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመተባበር ተደራሽነቱን ወደ 70 ወረዳዎች ለማስፋት በመስራት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስታወቀው፡፡ ሆኖም የተደራሽነት ችግር በተለይ በገጠራማ የክልሉ አካባቢዎች ማነቆ ሆኖብኛል ብሏል፡፡

በክልሉ በካሄድ ላይ ባለው ግጭት ምክንያት 5.2 ሚሊዮን (91 በመቶ) የሚሆነው ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግም ነው የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ቃል አቃባይ ቶምሶን ፒሪ የተናገሩት።

ቃል አቀባዩ «በክልሉ ረሃብ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሸጋገር ያሳስበናል» ማለታቸውንም የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል ።

በክልሉ እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ በረሃብ ምክንያት የሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ፤ የተጀመረውን የምግብ ድጋፍ አጠናክሮ ለማድረስ የተጠየቀው 203 ሚሊዮን ዶላር (166 ሚሊዮን ዩሮ) ገንዘብ በአስቸኳይ ሊቀርብ እንደሚገባም ድርጅቱ አሳስቧል።

በክልሉ 36 ወረዳዎች ሰብዓዊ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑ ይነገራል፡፡

መንግስት የሰብዓዊ ድጋን 70 በመቶ እንደሚሸፍን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe