መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ከመከላከያ ሰራዊት ጐን እንዲቆሙ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ

መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ከመከላከያ ሰራዊት ጐን በመሆን ለአገራችን ዘብ እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሲል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ።
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአገራችንን ሉአላዊነት ከማስከበር አልፎ ህዝባችን ድጋፍ በፈለጉበት መስክ ሁሉ በመሰማራት የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊታችንን መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው ብሏል፡፡
ምክር ቤቱ መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጐን በመቆም የአገራችንን ሉአላዊነትና አንድነት የምናስጠብቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ሲል በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe