ሲኖትራክ ተሸከርካሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱ ተገለጸ

የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ያለበትን የጥራት እና የቴክኒክ ችግር እስኪያሻሽል ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

የጥራት ጉድለቱ በየጊዜው የሰው ሕይወት ብሎም ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት በመሆኑ፤ አምራች ድርጅቱ ማሻሻያ እስከሚያደርግ ድረስ ተሸከርካሪው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉን የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዘሪሁን አሰፋ ለኢቢሲ ገልጸዋል።

ክልከላው ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም  ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ምንም ዓይነት የማስገቢያ ፈቃድ እንዳልተሰጠ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe