የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14/2013 ድምጽ መስጠት የማይቻልባቸውና ምርጫው ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ የተወሰነባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም መግለጹ የሚታወስ ነው።
ከዚህ ውስጥ ለምን ያህል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቀመጫዎች እና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ምርጫው እንደማይካሄድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዝርዝር አቅርቧል። በዚህም፦
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል – ለ4 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ13 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በኦሮሚያ ክልል – ለ7 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በአማራ ክልል – ለ10 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ9 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በደ/ብ/ብ/ህ ክልል – ለ16 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ22 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በሐረሪ ክልል – ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በአፋር ክልል – ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• ሶማሌ ክልል – ለ23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ72 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ በሰኔ 14 ምርጫ የማይካሄድባቸው ናቸው።
በአጠቃላይ ሰኔ 14 በ64 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ምርጫ #የማይካሄድ ሲሆን በእነዚህ አከባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ ይሆናል።

