ድምጻዊት ትዕግስት በቀለ ከ16 ዓመታት የውጭ አገር ኑሮ በኋላ የሙዚቃ ስራዋን ለማቅረብ ወደ ኢትዮጽያ ተመለሰች

ድምጻዊት ትዕግስት ሳቂታ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሰርታ ተወዳጅነትን ያተረፈች ድምጻዊት ናት፡፡ ከዚህ አልበም ውጭ ለአድማጭ ያደረሰችውና ተቀባይነትንም ያገኘችበትን አልበም አልሰራችም፡፡ በርግጥ በምትኖርበት አገር ከውጭ ዜጎች ጋር በመሆን ሙዚቃ የሰራች ቢሆንም፤ብዙ እንዳልተደመጠ ገልጻለች፡፡

ትዕግስት በቀለ ላለፉት 20ዓመታት ኑሮዋ በጣሊያን ነው፡፡

በኤሌክትራ አሳታሚ ድርጅት ታትሞ በተሰራጨውና ለእርሷም የመጀመሪያዋ ስራ በነበረው ሳቂታው አልበም በወቅቱ 50ሺ ብር እንደተከፈላትም አስታውሳለች፡፡ ያልወጣ ሁለተኛ አልበም እንዳላትም ከኢትዮፒካሊንክ ጋር በነበራት ቆይታ ላይ ተናግራለች፡፡

ድምጻዊቷ ከረጅም ዓመታት በኋላ ኢትዮጽያ የተመለሰችው መስከረም ሦስት የ90ናዎቹ ድምጻዊያን ያቀርቡታል በተባለው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ስራዎቿን ለማቅረብ እንደሆነ ተናግራለች፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe