ህወሃት ትግራይን ከከባባ ለማውጣት በሚል ያካሄደው ጦርነት ባለመሳካቱ በትግራይ የከፋ የኑሮ ውድነት መከሰቱ ተሰማ፤ 

 አንድ ሊትር ቤንዚል 515 ብር እየተሸጠ ነው ተብሏል፤

  የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥሞና ጊዜ ለትግራይ ለመስተጥ በሚል ባለፈው ሰኔ ወር ትግራይን ለቆ በወጣ ማግስት ህዝቡን ከከበባ ነፃ ለማውጣት በሚል በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ወረራ በመፈፀም ጦርነት ሲያካሂድ የቆየው ህወሃት ባለፈው ህዳር ወር በመከላካያ ሰራዊት ተመትቶ ወደ መቀሌ ከተመለሰ በኋላ በትግራይ የከፋ የኑሮ ውድነት መከሰቱ ተዘገበ፤

ቢቢሲ አማርኛ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሬ አግኝቻለሁ ባለው መረጃ መሠረት  የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ንሯል። ዋነኛ ምግብ የሆነውን ጤፍ፣ የስንዴ ዱቄት፣ በርበሬና ዘይት ዋጋ የማይቀመስ ሆኗል። ከአመት በፊት 100 ኪሎግራም ጤፍ ወደ 4 ሺህ 200 ብር ገደማ ይሸጥ ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን 7 ሺህ 600 ብር እየተሸጠ ነው።

አቅሙ ያላቸው አነስተኛ መጠን ያለው ጤፍ ገዝተው ከማሽላና ስንዴ ዱቁት ጋር በመቀላቀል እንጀራ ይጋግራሉ። ሆኖም ለበርካታ ነዋሪዎች ጤፍ መግዛት የማይታሰብ ነው። ከዚህ ቀደም በትግራይ ለምግብነት የማይውሉ ፍራፍሬዎች መንገድ ላይ እየተሸጡ ይገኛሉ፡፡

እነዚህን መከራዎች ለመወጣት ነዋሪዎች እንደ መኪና፣ የቤት እቃዎች እና ጌጣጌጦችን በኪሳራ ለመሸጥ የተገደዱ ሲሆን

በአንድ ወቅት 3 ሺህ 295 ብር ያወጣ የነበረ ባለ 21 ካራት የወርቅ ቀለበት በአሁኑ ወቅት ዋጋው ወርዶ በ700 ብር ይሸጣል። ከ800 ሺህ ብር በላይ ይሸጥ የነበረ መኪና ደግሞ 300 ሺህ ብር ሲሸጥ እየታየ  ነው።

ነዋሪዎች ንብረታቸውን ሸጠው ከጨረሱ በኋላ ወደ ልመና ይገባሉ። በየጎዳናዎቹ በርካታ ለማኞች አሉ፤ ከነዚህ ውስጥ ብዙዎች ልጆች የያዙ እናቶች ናቸው። የጤና ማዕከላትም መድኃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ቁሳቁሶች አልቆባቸዋል።

ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ህመምተኞች በመድኃኒት እጦት ምክንያት እየሞቱ ነው።

የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ያለባቸው ነዋሪዎች ደግሞ የጸረ ኤች አይቪ መድኃኒቶችን የሚያገኙት አንዳንድ ጊዜ ነው።

በትግራይ ዘንድ ይከበሩ የነበሩና የማህበረሰቡ መገለጫ የሆኑት ሃይማኖታዊ በዓላት፣ ሰርግና ሌሎች ድግሶች የሩቅ ጊዜ ትዝታ ሆነዋል።

አንድ ሊትር ቤንዚን ከጦርነቱ በፊት በነዳጅ ማደያዎች 22 ብር ይሸጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በሊትር 515 ብር እየተሸጠ ይገኛል። በከተማዋ ጋሪዎች ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እየዋለ መሆኑን ነዋሪዎች ይነገራሉ፡፡

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ የታወጀው የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ስምምነት በትግራይ ክልል እርዳታ እንዲገባና ለ17 ወራት ያህል የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት እልባት ሊያገኝ ይችላል የሚል ተስፋን ጭሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe