በሱዳን እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ አመፅ በየቀኑ እየተባባሰ በመሄዱ የሱዳን የሽግግር መንግስት የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጥቷል

መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን የነካ ይፈርሳል ይደቃል!!!!
በሱዳን የሚስተዋለው ነገር ይህን እውነት ያረጋግጣል!!!!
ዛሬ የካቲት 4/2013 ዓ.ም ወንድማችን Ustath Jemal እንደነገረን በሱዳን እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ አመፅ በየቀኑ እየተባባሰ በመሄዱ የሱዳን የሽግግር መንግስት የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጥቷል::
ይህ ህዝባዊ አመፅ ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት የሱዳን የሽግግር መንግስት #በሰባት (7) የሱዳን ግዛቶች ላይ የሰዓት እላፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል::
ህዝቡ ግን የተጣለውን እገዳ አልቀበልም በማለት ዛሬም አደባባይ ወጥቷል::
ሱቆች እና የንግድ ቤቶች እየተዘረፉ ነው::
ግጭት እና ትርምስ በየቦታው ይፈነዳል::
መንገዶች ይዘጋሉ:: ቃጠሎዎች እዚህም እዚያም አሉ::
መረጋጋት የሚባል ነገር የለም:: ትርምሱ ቀጥሏል::
የሽግግር መንግስቱ እጅግ ጨንቆታል:: ስለጨነቀውም የቀድሞ የሱዳን ባለስልጣናትን እያሰረ ይገኛል::
የአልበሽር ምክትል ፕሬዝዳንት የነበረውን አስረውታል::
ጋዜጠኞች ታፍነው ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ናቸው::
በአንፃሩ አልቡርሃን ቲቪ ላይ እየወጣ የቋጡን የባጡን ይቀባጥራል:: ችግር የለም ይላል:: ለማረጋጋት ይዳክራል:: ጉዳዩ ግን ለሱዳን ቀላል አልሆነም::
የኢኮኖሚ ችግራቸው ጣራ ነክቷል::
ወታደራዊ መንግስቱ የሲቪሉን አስተዳደር እንዳይውጠው የሱዳን ህዝብ በአንክሮ ይከታተላል::
የግብፅ ተላላኪ የሆነው የአልቡርሃኒ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት እጅግ ጭንቅ ውስጥ ገብቷል::
ኢትዮጵያም በግድቡ ዙሪያ ያሳየችው ጠንካራ አቋም ግብፅን እና ሱዳንን (በተለይ ግብፅን) እንዳሸበራት ኡስታዝ ጀማል አክሎ ነግሮናል:: ምን ይደረጋል? ጊዜው የኢትዮጵያ ነው!!! እነሱ እየተተረማመሱ ኢትዮጵያ ግድቧን ሞልታ ታጠናቅቃለች!!!! እንዲህ ማሰብ ባንፈልግም በኢትዮጵያ ግን ፈፅሞ አንደራደርም!!!!
ይሄን ለማየት የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!!!! ብርሃን ይታየኛል!!!! አንድ ብቻ እንሁን!!!! መንግስታችንም በዚህ ዙሪያ ይበርታ!!! የኢትዮጵያ እውነተኛ ትንሳኤ ቅርብ ነው!!!! ከዚህ በኃላ የምንፈራውም የምንፈርመውም ነገር የለም!!! ግድቡ ይሞላል ጠላት እርር ይላል!!!!
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe