በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ግጭት የተጠረጠሩ 62 ሰወች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በማምቡክና አካባቢው ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 62 ደርሷል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በማምቡክና አካባቢው ግጭት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 62 መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ ሀምደኒል ለኢዜአ እንዳሉት ማምቡክና አካባቢው ከጸጥታ ችግር ወጥተው በአሁኑ ወቅት ወደ ቀደመ መረጋጋት ተመልሰዋል፡፡

“በግጭቱ ምክንያት ተቋርጦ እና ተስተጓጉሎ የነበረው የአሶሳ- ግልገል በለስ፣ የግለገል በለስ- ማምቡክ፣ የግልገል በለስ-ፓዌ-ጃዊ-ማንኩሽና እና ሌሎችም ከተሞች የህዝብ ትራንስፖርት ትናንት እንደገና ተጀምሯል” ብለዋል፡፡

በፌዴራል እና በክልል ፖሊስ የተደራጀው ግጭቱን የሚመረምረው ቡድን ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽነር መሃመድ ጠቅሰዋል፡፡

እስከ አሁን በማምቡክና አካባቢው ግጭት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 50 ሲደርስ በጃዊ ግጭት ደግሞ ሌሎች 12 ሰዎች መያዛቸውን ተናግረዋል

ምንጭ – ኢዜአ

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe