በትዳር ውስጥ ገንዘብ ነክ ጉዳዮች

በትዳር ውስጥ ከሚገጥሙ ያለመስማማት ምንጮች አንዱ የወጪ አወጣጥ ስልት ነው፡፡ የወጪ አወጣጥ በምክክርና በሚገባ መመራት ካልቻለ ትዳርን እስከማፍረስ ያደርሳል፡፡ ታዲያ ገንዘብ ነክ ግጭቶች ትዳራችሁን እንዳይረብሹት ለማድረግ ተከታዮቹን ተግባራት ማከናወን ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን thebalance.com በተሠኘው ድረገጽ ሃሳባቸውን ያሠፈሩት ሼሪ ስትሪቶፍ ያስረዳሉ፡፡

  1. ሁለት የተለያዩ አካውንቶችና አንድ የጋራ የሒሳብ አካውንት ክፈቱ

‹‹የጋራ ባንክ አካውንት ወይስ ሁለት የተለያዩ የባንክ አካውንቶች ብንከፍት ይሻላል›› በሚለው ጉዳይ ላይ ባለትዳሮች መወሰን ይገባቸዋል፡፡ ውሳኔያቸው በመካከላቸው የሚፈጠሩ የጥቅም ግጭቶችን ለመቅረፍ ይረዳቸዋል፡፡ ስለዚህ ብትችሉ የየራሳችሁ የሒሳብ አካውንቶች እንዲሁም ሁለታችሁም የምታዙበት አንድ የጋራ የሒሳብ አካውንት እንዲኖራችሁ አድርጉ፡፡

  1. የገንዘብ አወጣጣችሁን አጢኑ

የገንዘብ አወጣጣችሁን ማስተካከል በእርስዎና በትዳር አጋርዎ መካከል የገንዘብ ማባከን ጭቅጭቆች እንዳይፈጠሩ ያደርጋል፡፡ አባካኝ ከሆኑ በትዳር አጋርዎና በልጆችዎ ሕይወት ላይ የኢኮኖሚና ስነ ልቦናዊ ጫናዎች መፈጠራቸው አይቀርም፡፡ እያንዳንዱ ወጪዎችዎን ከማውጣትዎ በፊት ባለቤትዎን ማማከርም ተገቢ ነው፡፡

  1. ቅድሚያ ለሚገባው ቅድሚያ ስጡ

ለእያንዳንዳችሁ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ምን እንደሆነ አስቀድማችሁ አቅዱ፡፡ ለምሳሌ እርስዎ ቤት እንግዛ የሚል ሃሳብ ቢኖርዎና ባለቤትዎ ደግሞ ለጡረታችሁ ገንዘብ መቀመጥ እንዳለበት ቢነግሩዎ ከሁለቱ ሊቀድም የሚገባውና ትልቅ ጥቅም ያለው ላይ ያተኩሩ፡፡

  1. የገቢያችሁን ዐሥር በመቶ ቆጥቡ

ቢያንስ የገቢያችሁን ዐሥር መቶኛ መቆጠብ አስፈላጊ ነው፡፡ ዋና ዋና ወጪዎቻችሁን ቦታ ካስያዛችሁ በኋላ የገቢያችሁን ዐሥር በመቶ የማስቀመጥ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በገንዘብ አወጣጥና አቀማመጥ ሥርዓታችሁ ላይ በግልጽ የመነጋገር ልማድ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe