በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃው የጠበቀ ላውንጅ ሊከፈት ነው

በኢትዮጵያ የኤርፖርት ላውንጅ የአገልግሎት ደረጃን ለማሳደግ ፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ እና ኤን.ኤች.ዋይ ጋር በሽርክና አጋርነት ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አደረጉ

ጥር 26 ፣2014 ዓም፡- በኤርፖርት የመንገደኞች መስተንግዶ አገልግሎት ከአለም ቀዳሚ የሆነው ፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ እና በኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የጉዞ ንግድ እና መስተንግዶ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆነው ኤን.ኤች.ዋይ መካከል በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዋና መዳረሻ በሆነው በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያለውን የተጓዦች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን እንደሚያሳድግ እምነት የተጣለበት የሽርክና አጋርነት ስምምነት አደረጉ፡፡

 ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ ፤ በያዝነው አመት መጋቢት ወር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተርሚናል 2 የሚከፈት ይሆናል፡፡ በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ቀዳሚ መዳረሻ የሆነው አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በየአመቱ ከ12 ሚሊዮን በላይ ተሳፋሪዎችን ያስተናገዳል፡፡ ይህ አዲስ የተመሰረተ የሽርክና አጋርነትም የፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕን የ24 ዓመታት የላቀ ልምድ እና የኤን.ኤች.ዋይን የሀገር ውስጥ የእንግዳ መስተንግዶ ልምድ በማዋሃድ በአየር ማረፊያ ውስጥ ያለውን የመንገደኞች አቀባበል እና የላውንጅ አገልግሎት ደረጃን የበለጠ ለማዘመን ያለመ ነው፡፡

 በ1000 ካሬ ሜትር ላይ የተንጣለለው ፕላዛ ፕሪሚየም ላውንጅ ኢትዮጵያ፤ በአንድ ጊዜ ለ325 እንግዶች አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ መስተንግዶ ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ ተደራጅቷል፡፡በዚህም መሰረት የተለያዩ ተጓዦችን ታላሚ ያደረጉ በርካታ አማራጮችንመ ይዞ ቀርቧል፡፡

 በመሆኑም አለም አቀፍ ተጓዦች ወደ መዳረሻቸው ከመሄዳቸው በፊት አረፍ የሚሉበት እና የሚገለገሉበት የተሟላ ፣ የቢዝነስ ማዕከል ፣ የገላ መታጠቢያ እና ማረፊያ ክፍሎች ፣ የሲጋራ ማጨሻ ላውንጅ ፣ ካፌ እና ሬስቶራንት የያዘ ነው፡፡ ላውንጁ ባህልን መሰረት ባደረገ ዲዛይን እና ልዩ በሆነ የኢትዮጵያ ምግብ አሰራር ደምበኞቹን ምቹ ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለማድረግ ታቅዶ የተሰናዳ ነው፡፡

የኤን.ኤች..ዋይ ባለቤት እና ዋና ስረ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ኑር ሁሴን ያሲን በበኩላቸው “ይህ ከፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ ጋር የተደረገ ስልታዊ አጋርነት በአፍሪካ ያለውን የጉዞ ሁኔታ እና ተሞክሮ ያበለፅገዋል፡፡በአዲሱ በቦሌ አየር ማረፊያ ላይ የሚጀምረውን ይህን የፕሪሚየም ላውንጅ አገልግሎት እስኪጀምርም በጉጉት እየጠበቅሁ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

 የፕላዛ ፕሪሚየም ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦራ ኢስቡላን ደግሞ “ሁሉን አቀፍ የሆነ እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኤርፖርት መንገደኞች መስተንግዶ አገልግሎትን በአፍሪካ ለማስፋፋት የያዝነው እቅድ አሁን ጅማሮውን አግኝቷል፡፡ ከኤን.ኤች.ዋይ ጋር በአጋርነት መስራት መጀመራችንም በአፍሪካ የበለጠ ማስፋፋት እንድንችል የሚረዳን በመሆኑ እጅግ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ መጥተን ስራ መጀመራችን ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎታቻንን ለማስፋፋት ለያዝነው ስትራቴጂ እና ራዕይ ማሳያ መሆን የሚችል ነው፡፡

ካለፉት ጥቂት አመታት ጀምሮ የአለም አቀፍ ቱሪዝም በኢትዮጵያ ትልቅ እድገት እያሳየ መጥቷል የኤን.ኤች.ዋይን የሀገር ውስጥ ልምድ እና የፕላዛ ፕሪሚየምን የ24 አመታት ልምድ በማዋሀድ በአየር ማረፊያ ጉዟቸውን ለሚያደርጉ አለም አቀፍ ተጓዦች ልዩ፣ አዲስ እና ምርጥ የሆነ ጊዜ አንዲኖራቸው ማድረግ እንደምንችል ልበ ሙሉ ነን፡፡ ይህ አጋርነት በአለም አቀፍ የአየር መንገድ ኢንዱስትሪ እንግዳ አቀባበል አገልግሎት ዘርፍ ላይ ቀዳሚ ለመሆን ያነገብነውን ራዕይ በመገንባት የሚደግፍ ነው፡፡”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe