በኢትዮጵያ 21 የታሸገ የማዕድን ውሃ ፋብሪካዎች ሥራ ማቆማቸው ተነገረ፤

በኢትዮጵያ 21 የታሸገ የማዕድን ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ሥራ እንዳቆሙ ተ ዘገበ። ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ሥራ ለማቆማቸው፣ የጥሬ ዕቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር፣ ሕጋዊ የሽያጭ ደረሰኞችን አለመጠቀም፣ መንግሥት በታሸገ ውሃ ላይ የሚጥለው ኤክሳይስ ታክስ እና ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ቅድሚያ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት አለማግኘታቸው በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

አሁን ምርት ያቆሙትን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ያሉት የታሸገ የማዕድን ውሃ አምራች ፋብሪካዎች 134 ሲሆኑ፣ ምርት በማምረት ላይ ያሉት ሌሎች ፋብሪካዎችም በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ እንዳልሆነ ዘገባው ገልጧል። የችርቻሮ ነጋዴዎች የታሸገ ውሃ ከፋብሪካ ዋጋው እስከ ሦስት እጥፍ ጨምረው  እመሸጥ በመጀመራቸው ህብረተሰቡ እያማረረ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe