በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ1,200 በላይ ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው ተሰናበቱ

ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሕወሃት ታጣቂ ቡድን ከደረሰበት ውድመት ሙሉ በሙሉ ባለማገገሙ እና የአጎአ እድል በመሰረዙ በሥሩ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በቀደመው አቅማቸው ልክ እያመረቱ አይደለም ተብሏል፡፡

በመሆኑም 1,214 የፓርኩ ሰራተኞች አሁንም ወደ ሥራ ገበታቸው እንዳልተመለሱ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

በፓርኩ ውስጥ ሥራ ላይ ካሉ ሼዶች መካከል በተለይ ካልሲ እያመረተ ወደ አሜሪካ ገበያ ይልክ የነበረው ፍአንላይ የተባለ የቻይና ኩባንያ ከጦርነቱ በኋላ አገግሞ ሥራ ቢጀምርም በጥቂቱ ብቻ እየሰራ በመሆኑ በርካታ ሰራተኞቹ ወደ ሥራቸው እንዳልተመለሱ ተሰምቷል፡፡

የወንዶች ሙሉ ልብስ እያመረተ ለአሜሪካ ገበያ የሚልክ የቻይና አሜሪካ ኩባንያ እና የሴቶች ቦርሳ እያመረተ እንዲሁ 95 በመቶ ለአሜሪካ ገበያ የሚያቀርብ ኩባንያ ሥራቸውን የተሻለ እየከወኑ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከሰጠቸው የቀረጥና ኮታ ነፃ እድል ኢትዮጵያን ማስወጣቷ ተከትሎ ሁለቱ ኩባንያዎች የገበያ ችግር እንደገጠማቸው ሸገር ከኩባንያዎቹ የስራ ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡

የገበያው ሁኔታ ሲስተካከልና በፓርኩ ውስጥ እየሰሩ ያሉ ኩባንያዎች በህወሃት አማካኝነት ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ አሁን የተቀነሱ ከ1,200 በላይ ሰራተኞች ወደ ስራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe