“እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።
ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።
ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።
አያይዘውም ተንታኙ ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።
በቴያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ በቅርቡ አሸባሪዎችን ለይቶ የማጣራት መረጃን የመለዋወጥ ሥምምንት መፈረማቸውን አዲስ አባበ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።
በዩናይትድ ስቴትስ በኩል ሥምምነቱን የፈረሙት፣ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ረዳት ሥራ አስኪያጅና የዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪዎችን አጣርቶ የመለየት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ቻርልስ ኤች ኬብል ሲሆኑ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የሀገሪቱ ብሄራዊ የሥለላና የደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ገብረሚካኤል ናቸው።
ሥምምነቱ ሁለቱ ሀገሮች የአሸባሩነትን ተግባር ለመከላከል ያላቸውን ብቃት ለማጠናከር ሲሉ መረጃ ለመለዋወጥ የሚችሉበትን አሰራር ይቀይሳሉ ይላል የቪኦኤ ዘገባ።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe