እናት ባንክ ለራይድ አሽከርካሪዎች  የብድር አገልግሎቶችን ሊያቀርብ ነው

እናት ባንክ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ምክንያት የራይድ አሽከርካሪዎች ላይ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ከግምት በማስገባት፣ ባንኩ የራይድ አሽከርካሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን አቅርቧል፡፡ እነዚህም የብድር ዓይነቶች እናት ራዕይ፣ እናት እፎይታ እና እናት ደራሽ ናቸው፡፡
እናት ራዕይ፡-
ይህ የብድር ማዕቀፍ በራይድ ውስጥ ተመዝግበው የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለራዕይ አሽከርካሪዎችን የሚመለከት ሲሆን፣ ብድሩም ለአዲስ መኪና መግዣ የሚውል ይሆናል፡፡ በመሆኑም የዚህ የብድር ተጠቃሚ ለመሆን ለመግዛት ከሚታሰበው የመኪና ዋጋ ውስጥ 30 በመቶውን በአንድ ዓመት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ የብድር መክፈያ ጊዜው እስከ አምስት ዓመት የሚቆይ ይሆናል፡፡
እናት እፎይታ፡-
ይህ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ የራይድ አሽከርካሪዎች ለዓመታዊ ግብር ክፍያ፣ ለመኪና ጥገና እና ተያያዥ ወጪዎች ለመሸፈን የሚውል ነው፡፡ የዚህ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን አሽከርካሪዎች በትንሹ ለሦስት ወር የእናት ባንክ ደንበኛ መሆንና በቋሚት መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ የብድር አገልግሎት የራይድ አሽከርካሪዎች እስከ 10,000.00 (አስር ሺ) ብር የሚደርስ ብድር ማግኘት ይችላሉ፡፡
እናት ደራሽ፡-
ይህን የብድር አገልግሎት የሚጠቀሙ የራይድ አሽከርካሪዎች፣ ለተዘዋዋሪ የሥራ ማስኬጃ የሚያውሉት እስከ 1000.00 (አንድ ሺ) ብር የሚደርስ ብድር ነው፡፡ ይህ የብድር አገልግሎት አሽከርካሪዎቹ የራይድ የትራንስፓርት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የሚጠቀሙበት ብድር ሲሆን፣ ምንም ዓይነት የወለድ ምጣኔ የማይታሰብበትና ለተወሰደው ብድር በቀን አንድ ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ የሚታሰብበት ነው፡፡
ስለ ሃይብሪድ ዲዛይንስ
ሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃላ/የተ/የግ ማህበር በሥራ ፈጣሪዋ ወጣት ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ በ2007 ዓ.ም የተቋቋመ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሲሆን፣ በዋነኛነትም የአዲስ አበባ ከተማ መሠረታዊ ችግር የሆነውን የትራንስፓርት ችግር በመቅረፍ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በዚህም ሒደት ውስጥ ዘርፉን በማዘመን ራይድ የተባለውን አገልግሎት ያስተዋወቀ ተቋም ነው፡፡ ድርጅቱ የከተማይቷን የትራንስፓርት ችግር በመቅረፍ ሒደት ውስጥ በአገሪቷ ያለ ስራ የተቀመጠን ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ወደ ሥራ በማስገባት ለበርካቶች የሥራ ዕድልን የፈጠረ ተቋም ነው፡፡
ስለ እናት ባንክ
ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት በአሥራ አንድ እንስት ባለራዕዮች ተቋቁም በተለይም በአገሪቷ የባንክ ስርዓት ውስጥ እምብዛም ትኩረት ያልተሰጣቸው ሴቶችን ታሳቢ በማድረግ ወደ ሥራ የገባ ተቋም ነው፡፡ ባንኩ ከ18 ሺ በላይ ባለ አክሲዮኖች ያሉት ሲሆን፣ ከ64 በመቶ ባለ አክሲዮኖች ሴቶች ናቸው፡፡ የባንኩ የባለፈው ዓመት ያልተጣራ ትርፍ ከ289 ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉም ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe