እናት ባንክ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ጋር  ፍሬያማ  ውይይት ማድረጉን አስታወቀ

እናት ባንክ “የታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ” አካል ከሆኑት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ጋር በዛሬው ዕለት በኢንተርሌግዤሪ ሆቴል ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ጋር በትብብር ስለባንኩ አጠቃላይ መረጃ እና ባንኩ ለዲያስፖራ ማህበረሰብ ያቀረባቸውን የዲያስፖራ የባንክ አገልግሎቶች  ውይይትና የምሳ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

Diaspora Participant
Diaspora Participant

እናት ባንክ “የታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ” አካል ከሆኑት የዲያስፖራ  ማህበረሰብ  ስለባንኩ አጠቃላይ መረጃ እና ባንኩ ለዲያስፖራ ማህበረሰብ ያቀረባቸውን የዲያስፖራ የባንክ አገልግሎቶች  አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ እና ፍሬያማ  ውይይት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

እናት ባንክ አዲስ አበባ የሚገኙትን ቅርንጫፎቹን ለሀገራቸውና ለማህበረሰባቸው በተሰማሩበት መስክ ትልቅ አስተዋጽኦ ባበረከቱ ሴቶች የመሰየምና የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን እውቅና የሚሰጥበትን ሂደት በመቀጠል ሰሞኑን ላምበረት መናሕሪያ ፊት ለፊት የከፈተውን 94ኛ ቅርንጫፉን በነፍሳት ኢኮሎጂና ፊሶሎጂ የምርምር ሥራዎች በመሥራት የሚታወቁ ሴት ሳይንቲስትና የአለምአቀፍ በአይን የማይታዩ ነፍሳት ምርምር ማዕከል መሥራችና ዳይሬክተር በሆኑት ደ/ር ስገነት ቀለሙ  ሰይሟል፤

እንዲሁም 95ኛ ቅርንጫፉን ፊጋ አካባቢ በኦቲዝም የተጠቁ ልጆችን በመንከባከብ በሚታወቁት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ስም ቅርንጫፍ በመሰየም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በመግለፅ ደንብኞች  ቅርንጫፎቹን እንዲጎበኙ እና በምንታወቅበት እናታዊ መስተንግዶ  የባንካችንን አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ጋብዟል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe