የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ማናቸው?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አመራር ቦርድ አቶ መስፍን ጣሰውን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደሾመ አስታወቀ፤

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አመራር ቦርድ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ሃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉትን አቶ  መስፍን ጣሰውን የአየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል::  አቶ   መስፍን በአየር መንገዱ ለ38 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፣ ቀደም ሲልሹ በአየር መንገዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገና እና ኢንጂነሪንግ እንዲሁም የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።

አቶ   መስፍን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በተሾሙበት በዚህ  ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 ከመቶ ድርሻ በያዘበት የቶጎ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

የአየር መንገዱ ቦርድ በአዲሱ የቦርዱ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ ስርየቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉን፣የብሔራዊ መረጃናደህንነት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህን፣እንዲሁም የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ የሆኑትን ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳን ጨምሮ አዳዲስ የቦርድ አባላት ተሹመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe