የኢትዮጵያውያ ምሁራን ከህዳሴው ግድብ ጋር በተገናኘ ከግብጽ አቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ ያነሰ ሚና እያበረከቱ እንደሆነ ተገለጸ።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በሚካሄደው የህዳሴው ግድብ ጉባኤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪው ፕሮፌሰር በላይ ስምአኔ ባቀሩበት ጥናታዊ ፅሁፍ እንዳሉት፣ በተለይ በአባይ ወንዝ ሃብት ላይ ለሶስቱ ሀገራት የሚኖራቸው እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አግባብ ገና ጥናት የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።

እስካሁን ድረስ ታላቁ የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች የሶስቱን ሀገራት (ኢትዮጵያዊ፣ ሱዳንና ግብፅ) ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብለው የተለዩ ነገሮች ቢኖሩም የተሟሉ ናቸው ማለት ግን ይቸግራል ብለዋል።

የህዳሴው ግድብ መገደብና አገልግሎት መስጠት መጀመር ሀጋራቱ ተጠቃሚ ሊሆኑባቸው የሚችሉባቸው ዘርፎችን በዝርዝር የተቀመጡ አይደሉም ነው ያሉት።

በተለይ በግብፅ የህዳሴውን ግድብና በአባይ ውሃ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተጠቃሚነት በዘላቂነት አስጠብቆ ለመቆየት በርካታ ቁጥርና ሚና ያላቸው ምሁራን እንዳሏት አውስተዋል።

ስለሆነም ከግብፅ የአባይ ጉዳይ ተማራማሪዎችና ተከራካሪ ምሁራ ብዛት ጋር ሲነፃፀር የኛ ሀገር ምሁራን በቁጥርም በሚናም አናሳ ናቸው ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ አክለውም የአባይን ወንዝ ተፋሰስ ሊያጎለብቱ የሚችሉ የትኞቹ የተፈጥሮ ሃብት እቀባ ስራዎችን መተግበር እንደሚገባ በጥናት በግልፅ መታወቅ ያለባቸው ናቸው ሲሉ አስታውቀዋል።

በመሆኑም በህዳሴው ግድባችንና በአባይ ወንዝ ላይ ካሉን ተመራማሪዎች፣ አጥኚዎችና ተከራካሪ ምሁራን በተጨማሪ አዳዲስ ባለሙያዎችን ማፍራት ይገባናል ብለዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe