የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት አገልግሎት በግማሽ ቢሊየን ብር 3 ሺ ኮንቴነር ገዛ!

በአለም ላይ የተፈጠረው የኮንቴነር እጥረት በስራው ላይ ያሳደረበትን ጫና ለመቅረፍ የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት እና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) በአፋጣኝ ግዥ 3 ሺ የተለያየ የመያዝ አቅም ያላቸውን ኮንቴነሮች ገዛ፡፡የኢባትሎአድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል እንደተናገሩት የተፈጠረው ችግር እስከ 2 አመት ሊቆይ እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ ብለው፡፡

በኮንቴነር እጥረት ምክንያት የመርከብ ጭነትም በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውሰዋል፡በመሆኑም ኮንቴነር ተከራይቶ እና ለጭነት ከፍሎ እቃ ማጓጓዝ እጅግ ውድ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሮባ ችግሩን መቅረፍ የሚቻለው በራስ ኮንቴነር መሆኑ በተሰራ ጥናት መረጋገጡን እና እጅግ አትራፊ መሆኑ በመታወቁ በፈጣን ግዥ 3 ሺ ኮንቴነር ተገዝቷል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት እና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) በአጭር እና መካከለኛ እቅድ በቻይና ወደቦች ለረጅም ጊዜ የተቀመጡ ጭነቶችን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አጓጉዞ እንደሚያጠናቅቅ ገለፀ፡፡

ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በአለም ላይ ከፍተኛ የኮንቴነር እጥረት በመከሰቱ በርካታ ጭነቶች በወቅቱ የንግድ መሪ ከሆነችው የቻይና ወደቦች መነሳት አለመቻላቸው በዘርፉ ተግዳሮት መሆኑ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያም የዚህ ጫና አካል መሆኗን በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ሆኖም ችግሩን ለማቃለል ኢባትሎአድ በአዲስ ስትራቱጂ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ለዚህም እንዲረዳው CMA-CGM እና MSC ከተባሉ አለም አቀፍ የመርከብ ኩባንያዎች ጋር ውል ያሰረ ሲሆን፡፡እነዚህ ሁለት የመርከብ አንቀሳቃሾች ወደብ ላይ የተከማቹ የኮንቴነር ጭነቶችን እንዲሁም አዲስ ትእዛዞችን ለማጓጓዥ እንደሚሰሩ ታውቋል፡፡በተጨማሪም የኢባትሎአድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ እንደተናገሩት ወደ አራት የሚሆኑ የኢትዮጵያ መርከቦች መዳረሻቸውን ወደ ቻይና በመቀየር እያንዳንዳቸው ቢያንስ 1 ሺ ኮንቴነር ይዘው ወደ ጅቡቲ ይመጣሉ ብለዋል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe