የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባንኮች የኢንፎርሜንሽን ቴክኖሎጂን በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ አዘዘ

የፋይናንስ ዘርፍ ተቆጣጣሪው ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) በቅርቡ ያወጣው መመሪያ እንደሚገልፀው የኢንፎርሜንሽን ቴክኖሎጂን ትግበራውን በሁለት አመት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንዲያደርጉ ባንኮችን ያዛል፡፡
ስለጉዳዩ ያናገርናቸው የ ባንክ አመራሮች መመሪያው ተገቢነት ያለው እና አሁን ከሚሰራበት አተገባበር በተላቀቀ እና ወጥነት ባለው መልኩ መሄድ የሚያስችል ነው ብለውታል፡፡
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ ሂደት ብቃትን፣ ውጤታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል የሚለው የመመሪያው መግቢያ፤ ባንኮች ቢያንስ ወሳኝ የስራ ሂደታቸውን በቴክኖሎጂ ማገዝ ይኖርባቸዋል በማለት ያክላል፡፡
ለትገበራውም የጠራ የስራ እቅድ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶችን በማድረግ ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል ይላል፡፡ ለትግበራውም እስከ ሁለት አመት ጊዜ የሰጠ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe