የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከአስር ዓመት በኋላ 2200 በላይ ይደርሳል ተባለ

በኮረና ቫይረስ ሳቢያ የሀገራት ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ መኮማተሩ ይታወቃል፤ አስቀድመው እድገት ይዘመዘገባል በሚል እቅድ ያወጡ ሀገራት አሁን ከኮረና መከሰት በኋላ እቅዶቻቸውን እየከለሱ ስለመሆኑ ተሰምቷል፡፡

Read also:ሁለት አየር መንገዶች በኪሳራ ስራ አቆሙ

ከእነዚህ ሀገራት መሀከል አንዷ ሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ የ አስር ዓመት ብሔራዊ የኢኮኖሚ እወቅድ ሰሞኑን ተከልሶ ይፋ ሆኗል፤ በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነር ፍፅም አሰፋ/ዶ/ር / ሰብሳቢነት ከሚመለከታቸው የዘርፉ ተዋንያን ጋር በተደረገው ምክክር መጨረሻ ላይ ይፋ የተደረገው እቅድ በየዓመቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቢያንስ በ10.2 ከመቶ ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን የሀገሪቱ ዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን ካለበት 900 ዶላር ወደ 2248 ዶላር እንደሚያድግ ተተንብዮአል፤

Read also:‹በወረርሽኙ ምክንያት የኢኮኖሚ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል› ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  

ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት የኢትዮጵ የነፍስ ወከፍ ገቢ 200 ዶላር የነበረ ሰሆን የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እቅዳችን ህዝቡ በቀን ሁለቴ ምግብ እንዲመገብ ማድረግና ገቢውን 1000 ዶላር ማድረስ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe