የእንግሊዙ ኖቲንግሃም ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የክብር ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱ አነጋጋሪ ሆነ

ግለሰቡን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ቸልተኝነት ቁጣን ፈጥሯል፤

የእንግሊዙ የኖቲንግሃም ዩኒቨርሲቲ ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የክብር የፕሮፌሰርነት ማእረግ መስጠቱ አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው፤

የዩኒቨርሲቲው የህክምና ሳይንስ ፋካሊቲ የሀምሳኛ አመት ክብረ በአሉ ባከበረበት በዚህ ወቅት ለዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የፕሮፌሰርነት መአርግ መስጠቱ የተቋሙ ተመራቂዎችን ስኬት ማሳያ ነው ሲል  ገልጿል።

በሌላ በኩል በርከት ባሉ ምሁራን እና የአለም ማህበረሰብአባላት ከኮቪድ 19 መከሰት ጋር ተያይዞ ባሳዩት ከፍ ያለ ቸልተኝት የሚወቀሱት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኮረና ምክንያት በርካታ ሰዎች እየሞቱ በነበረበት ወቅት የቻይና መንገስትን ወግነው በሽታውን ወረር       ሽን ብለው ለመሰየም ሲያንገራግሩ እንደነበር በመጥቀስ በርካቶች የዩኒቨርሲቲውን እርምጃ ኮንንዋል፤

ዶ/ር ቴዎድረሮስ አየኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የገቡበን የህልውና ጦርነት ለመመከት ትግል በሚያደርጉበት ወቅት ከአሸባሪው ህወሃት ሚስጥራዊ ድጋፍ ማደረጋቸው በስፋት ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርንት ጋር ተያይዞ ሃየህወሃት ሀይሎች በአማራና በአፋር ክልሎች ከ2700 በላይ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማትን ሲያወድሙ አይተው እንዳላየ ያለፉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የህወሃት ሀይሎች ከፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር ተያይዞ በጥምር ሊጠየቁ እንደሚገባ ዓለም አቀፍ ዘመቻዎች መጀመራቸው ታውቋል፤

በቅርቡም በዓለም የጤና ድርጅት ድረ ገጽ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰውን የጤና ተቋማት ውድመወት የመረጃ ዳታ እንዲጠፋ ማድረገቸው ይፋ ቢደረግም የኢትዮጵያ መንገስት ጉዳዩን በተመለከተ አለም አቀፍ አጀንዳ በማድረግ  ተጠያቂነት እንዲኖር ከመስራት ይልቅ  በግለሰቡ ላይ እያሳየ ያለው ቸልተኝነት እያስተቸው ስለመሆኑ ይነገራል።

ዶክተር ቴድሮስ ዩንቨርሲቲው ላደረገላቸው የክብር ሽልማት በማመስገን ለቀጣይ ከፍተኛ ስራ ለመስራት አጋዥ ነው  ማላታቸው የተዘገበ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ተጋበር በኢትዮጵያውያንና በትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን መቀስቀሱ ነው የተሰማው፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe