ጃዋር መህመድ
ጃዋር መሀመድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስሙ እየገነነ የመጣው ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በኋላ ነው፡፡ ጃዋር የኦሮሞ ብሔርተኝነትን አቀንቃን ሲሆን በተለይም ከ2008 የኦሮሚያ ወጣቶች አመፅን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማደራጀት እንደመራ ራሱም በሰጣቸው ቃለ ምልልሶች ገልጧል፤ጃዋር በ2009 በመላ ሀገሪቱ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከመሰረቁ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደነበረው ወደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ በሰጣቸው ቃለ ምልልሱ ላይ ተናግሯል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ አሜሪካ ባደረጉት ጉዞ በሜኔሶታ ግዛት በተደተረገው የዘቀባበል ስነ ስርኣት ላይ ይፋዊ ያልሆነ እውቅና ያገኘው ጃዋር ወደ ሀገር ቤት ሲገገባ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎለታል፤ ጃዋር በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ምን መደረግ እንዳለበትና እንደሌለበት የሚናገርበትን የኦኤም ኤን የተባለውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከመሰረተ በኋላ ተፅእኖ ፈጣሪ መሆኑን ብዙዎች ያምናሉ፡፡ በቴሌቪዥኑ ላይ በሚሰጣቸው ማብራሪያዎችና አስተያቶች አነጋጋሪነቱን ማስጠበቅ ችሏል፡፡
ጃዋር ከለውጡ በኋላ የመንግስትን የፖሊሲና የህግ አካሄዶች በግልጽ ከመተቸትም አልፎ ተጋባራዊነቱን በግልጽ በመንቀፈፍ ህጎቹንና አፈፃፀሞቹን ማስቀልበስ መቻሉን የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ በነበረበት ሰዓት በኦኤም ኤን ቴሌቪዥን ላይ ዕጣው መውጣት እንደሌለበት የተናገረው የወቅቱ መነጋገሪያ ነበር፡፡ የከተማው አስተዳደር የጃዋርን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በማለት ዕጣው እንዲወጣ ቢያደርግም ይህንኑ ድርጊት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ 22 ከተሞች በአንድ ቀን እንዲወጡ በማስደረግ የኮንዶሚኒየም እጣው ለደረሳቸው ባለዕድለኞች እንዳይተላለፉ ማስደረግ እንደቻለ ይነገራል፡፡
ጃዋር በ2011 የከተማ አስተዳደሩን አቋም ብቻ ሳይሆን ያስቀየረው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም የቤቶቹ ዕጣ አወጣጥ ላይ ቅሬታ እንዳለውና ለባለዕድለኞች እንዳይተላለፉ የሚጠይቅ መግለጫ እንዲያወጡ ግፊት ማድረጉን በመጥቀስ የጃዋር ተፅእኖ ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል የሚሉ ተንታኞች አሉ፡፡ ጃዋር ‹በዚህች ሀገር ላይ ያለው ሁለት መንግስት ነው፤ አንዱ ዶ/ር አብይ የሚመራው ሲሆን ሁለተኛው የቄሮ መንግስት ነው› በሚል የሰጠው አስተያየት እውነታውን ያሳያል ሚሉ አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ‹በዚህች ሀገር ላይ ያለው ጠቅላይ ሚኒስትስር አንድ እኔ ብቻ ነኝ ፤ ቢያንስ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ› በማለት ስልጣኑ የእሳቸው ብቻ እንደሆነ ቢናገሩም በተለያ ጊዜ በጃዋር አቀንቃኝነት የሚወጡ ህጎችና አፈፃፀሞች የጃዋርን ይሁንታ ስለማግኘታቸው ብዙዎች መጠየቅ ጀምረዋል፡፡
በቅርቡም የትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት ስድስት ወራት ሳካሂድ የቆየሁት ነው በማለት ይፋ ያደረገው የትምህርትን ፍኖተ ካርታ በተለይ ከቋንቋ ጋር ተያያዘውን ክፍል ጃዋር አምርሮ የተቸው ሲሆን በማግስቱም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይህንኑ የሚያጠናክር መግለጫ አውጥቷል፤ ትምህርት ሚኒስቴርም ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ ያወጣሁት ፍኖተ ካርታ ምክረ ሀሳብ ነው ለማለት ተገዷል፡፡
ጃዋር በሲዳማ ህዝብ የራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ጥያቄ ዙሪያም ግልፅና የማያሻማ አስተያየቱን መስጠቱ ይታወሳል፡፤ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት በተከበረው የጨምባላላ ክብረ በዓል ላይ መልዕክቱን ያሳስተከላለፈ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ በሀይል የሚደረግ የመብት ጥያቄ እንደተለመደው በሀይል ይመለሳል፤ እንደ ሶማሊያ ይሆናል ቢሉም የኋላ የኋላ የሲዳማ ህዘብ የህዝበ ውሳኔ የጥያቄው የ60 ሰዎችን ህይወት ቀጥፎም ቢሆን ምላሽ አግኝቷል፡፡
ጥሩ የመናገር ችሎታ፤ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አጣምሮ የተካነው የ34 ዓመቱ ጃዋር መሀመድ የየኦሮሞ ብሔርተኝነትን በማቀንቀን የፌደራሊዝም ስርዓቱ እንዳይነካ ከሚታገሉ የኦሮሞ ሔርተኞች መሀከል ይጠቀሳል፡፡
‹‹የዓመቱ ሰዎች››
