የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ  ጥሪ

የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ  ጥሪ ለሁሉም የቀረበ ፈተናም መልካም እድልም ሊሆን ይችላል

አክሊሉ ወንድአፈረው ethioandenet@bell.net

ሰኔ 10፣ 2020 (ጁን 17,2020)

 

የጠቅላይ ሚኒሰቴር አብይ ስኔ 5፣ 2012 (ጁን 12፣ 2020) ለህዝብ በቴሊቪዥን ሬዲዮና ማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ያስተላለፉት መልእክት አራት  ቁልፍ  ቁም ነገሮችን  ያዘለ ነው፡

ኮሮናን ለመዋጋት፣ኢኮኖሚውንና ማህበራዊ ቀውሰን ለማሰወገድ፣ በሀገር ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን የምግብ አጥረት፣ አደጋ ለመቋቋም ቀጣዩን ምርጫ ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ተአማኒ በማድረግ ላይ ተቃዋሚው፣ የሲቪክ ማሕበረስቡና፣ የሐይማኖት ተቋማትን እንዲሁም  ታዋቂ ኢትዮጰያውያን  አንዲተባበሩ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

Read also:አቶ ስዩም መስፍን የባንክ ሂሳባቸውን ለማስመርመር ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

አንድ የሀገር መሪ ተራ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪቨን ፐሮግራም ዜና አቅራቢ አይደለምና በቴሊቪዥን ወይም በሌላ መገናኛ ብዙሀን ብቅ ብሎ መልእክቱን ሲያስተላልፍ  ቢያንስ ሶስት  ታላላቅ ነገሮችን ያመላክታል፤

·         የሚተላለፈው መልእክት በመንግስት ደርጃ ከፍተኛ ክብደት የተሰጠው  መሆኑን

·         ከዚህም የተነሳ በዛ ያሉ የህዝብ መገናኛዎች  መልእክቱን እንዲያስትላልፉት ማለትም ብዙ ህዝብ እንዲሰማውና አንዲመለከተው  እንደተፈለገ

·         መልእክቱ ሳይሽራረፍና ሌላ ቅመም ሳይጨመርበት በቀጥታ ለአድማጭ ተመልካቸች አንዲቀርብ  መፈለጉን ያመለክታል

ጠቅላይ ሚኒሰቴሩ ንግግር ይዘትና የተጠቀሙበት የመገናኛ ብዙሀን  አይነት የዚሀ ንግግራቸው ትኩረት  አንድ የህብረተስብ ክፍል ብቻ ሳይሆን በተነሱት አራት ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ህዝብ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሌሎችም ባለደርሻዎች የአርሳቸው ንግግር  የተኮረባቸው ክፍሎች እንደሆኑ ያሳያል

Read also:ኢትዮጵያ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ሲቀር የ25 ቢሊዮን ብር የመንገድ…

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቴሌቪዥን፣ የሬዲዮም ሆነ የሶሻል ሚዲያን  ሀያል መሳሪያነት ጠንቀቀው ያውቃሉና  በዚህ  ንግግራቸው የአርሳቸውን መልአክት  ሳይቀነስ ሳይጨመር አንደወረደ የማሰጨበጥ ፍላጎትና ጥረታቸው እርሳቸው ባነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች  ዙሪያ የሚደመጡ  ተቃራኒ እመላካክቶችን (ለምሳሌ አብይ  ፍላጎቱ ስልጣኑን ማጠናከር ነው፣ ወደ አምባገነነነት አየገሰገሰ ነው፣ ምርጫውን ነጻና ተአማኒ ለማድረግ ፍላጎት የለውም ወዘተ የሚሉትን  ) በአስቸኳይ ለመፋለም ወይም ለማምከን ያላቸውን ጉጉት  ያሳያል።

የአጀንዳዎቹን አጅግ ወቅታዊነትና በህዝብ ውስጥ ዋና ዋና መነጋገሪያ መሆናቸውን በግናዛቤ ውስጥ ሰናስገባ ደግሞ የተናገሩትን ተግባራዊ አለማድረግ በጠቅላይ ሚኒሰቴሩ ተአማኒነትና  በሚመሩት የፖለቲካ ድርጅት ተቀባይነት ላይ ሊያሰከትል የሚችለውን እደጋ በግልጽ ያመላክታል። ሆኖም ግን ቀድመው በነዚህ አጀንዳዎች ላይ እንተባባር ብለው የስላም አጃቸውን እንደዘረጉ ማወጃቸው በፖለቲካው መድረክ የአጥቂነት ቦታ ላይ ለመቀመጥ መንቀሳቀሳችቸውን ያሳያል።

በአንጻሩም በተነሱት ጉዳዮች ላይ  በጋራ አልሰራም ፣ አልተባበርም በሚል የፖለቲካ ድርጅት ላይም የሚያደርሰው  አሉታዊ ተጻእኖ  ከፍተኛ እንደሚሆነ  መረዳት አይክብድም።

Read also:ሁለት አየር መንገዶች በኪሳራ ስራ አቆሙ

ከዚህም የተነሳ የፖለቲካ ድርጅቶች  በተነሱት ጉዳዮች ይዘት ላይ ክሚያነሱዋቸው መሰራታዊ  ሙግቶች  በተጨማሪ አንዱና ትልቁ ትንቅንቅ የህዝብን ልብና ቀልብ ለማሽነፍ የሚደረገው ትግል ሆኖ ይታያል።

ከህዝብ ግንኙነት ሩጫና ፍጥጫ  ባሻገር፣ግን  ጠቅላይ ሚኒሰቴር አብይ ያቀረቡት ጥሪ በተግባር ከተተረጎመ ለሀገርና ለወገን ካለው ጠቀሜታ አንጻር በመልካም ጎኑ መታየት የሚችል ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፉት ጊዜያት ይፈጸማሉ እየተባለ ቃል የተገባላቸውና  በመጨረሻ ግን ደብዛቸው የጠፋው የሚያጓጉ ጉዳዮች ብዙዎች ናችወና የትላንቱ አዙሪት ውስጥ ላለመውደቅ አሁንም አንዳንድ ቁልፍ ጉዳዮችን በግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ብቻ ሳይሆን ገና ከጅምሩ በተግባር ማዋል  ለሂደቱ ማማርም  ሆነ ለውጤቱ መሳካት  አስፈላጊ ይሆናል። ከነዚህም ውስጥ፤

·         ሀገራችን የሚባክን ጊዜ ህዝብም “ቆይ አስኪ፣ ረጋ ብለን እንየው” የሚል አንጀት የላቸውምና የተባሉትን አጀንዳዎች በጥልቀት ለመነጋገርና ተግባራዊ  መፍትሄዎችን ለመሻት  የሚያስችለው ጉባኤ በአስቸኳይ  አንዲካሄድ ያስፈልጋል፣

·         ጉባኤው ካሁን በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው የተለመዱትን ጥቂት ድርጀቶች ብቻ ሳይሆን  ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶችና ሌሎችም  ባለደርሻዎች ማጠቃለል ይኖርበታል፤፡ ይህ ካልሆነ ጥረቱ ሁሉ ገና ከመጀመሪያው ውድቅ ሊሆን ይችላል። ቀጣይ የመቀራረብ ፍላጎትንም ይበልጥ አዳጋች ያደርጋል።ባጭሩ የጉባኤው ሁሉን አሳታፊነት አማራጭ የለውም።

·         የተጠቀሱትን  ዋና ዋና አጀንዳዎች  በጋራ ተነጋግሮ መፍትሄዎችንም ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው አልፎ አልፎ  ሚካሄድ ድንገተኛ የጥቂት ሰአታት ውሱን ውይይት   (adhoc meeting) ሳይሆን፣ ቀጣይነት ያለው  ባለድርሻዎችን ሀሳብ ከማፍለቅ ፣ ጀምሮ መግባባት ላይ የተደረሰበት የተግባር አቅድ በማዘጋጀት፣ በተግባራዊነቱ ላይ መሳተፍና እቅዱ ወደ ተፈለገው ግብ አየተጓዘ  መሆኑም በሚገመግም ሂደት  (monitoring and evaluation) ውስጥ ትርጉም ባለው መልክ መሳተፍን የሚያጠቃልል ሊሆን ይገባል።

·         ከተፎካካሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ጋር መስራት፣ መደራደርን፣ ሰጥቶ መቀበልንና የተለያዩ አማራጩችን በትእግስት መመርመር ሰለሚጠይቅ ሁሉም ባለደርሻዎች፣ በተለይም  መንግስት ለዚህ ሂደት ሰነልቦናዊ  ዝግጅት ሊያደርግ ይገባል።

Read also:የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከአስር ዓመት በኋላ 2200 በላይ ይደርሳል ተባለ

·         ሀገራችንም ሆነች ህዝባችን ዛሬም በአንድ በኩል  በውስብስብ  ፈተና የተወጠሩበት አዳጋ  በሌላ በኩል ደግሞ  የወደፊት እጣ ፈንታችንን  መሰረታዊ በሆን መልክ በጋራ  አስተዋጻኦ መቀየር  የሚያስችል  መልካም የታሪክ አጋጣሚ  ላይ ይገኛሉ።   መንግስትም ሆነ ሌሎች ባለደርሻዎች  የትኛውን አማራጭ እንደሚመርጡ በተግባር የሚታይ ቢሆንም ይህን መልካም አጋጣሚ እንድገና እንደማያበላሹት ግን የብዙዎች ተስፋና ምኞት ነው።

ጠቅላይ ሚኒሰቴር አብይ መጽሀፍ የጻፉለት አቶ ክድር ሰተቴ በደርግ ጊዜ የሆን ነገር ተናግረሀል  ተብሎ  ጂማ  ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ከሴ የሚሉት አስር ቤት ይወረወራል። አና እዚያ የነበሩ ሌሎች አስረኞች ፣ አቶ ከድርን አንተ ደግሞ ምን አድርገህ ታስርክ?  ምን እዚህ አመጣህ?  ብለው ይጠይቁታል። እርሱም መልስ ሲስጥ “ እኛ የምንለው ለፉገራ እነርሱ የሚሉት የመግደል ሙከራ” ይል ነበር ይባላል። 

አሁን ይካሄዳል የተባለው የመንግስትና ሌሎች ባለድርሻዎች ጉባኤም  የከድር ሰተቴንና የአሳሪዎቹን  እይታ የሚያስታወስን እንደማይሆን ተስፋ እናድርግ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe