“ያን ሲያማ ያን ሲያማ ወገኔ ለእኔ ብለህ ስማ” ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ

ከሶስት ዓመት በፊት  በተባባሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወጣቶችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እየመራቸው በመሆኑ ‹አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግበት ይገባል› ሲሉ ንግግር አድርገዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በግርድፉ ሲታይ በወቅቱ በኦሮሚያና የአማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚመራው ማህበራዊ ሚዲያው በመሆኑ አንድ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል የሚል አንድምታ አለው፡፡ ሰሞኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት በጽ/ቤታቸው በኩል አውጥተዋል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ሃሳብን በነፃነት የመግለጫ አንዱ መንገድ ተደርጎ በመላው ዓለም ተቀባይነትን ያገኘ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

እርግጥ ነው ማህበራዊ ሚዲያዎችን በአግባቡ ባለመጠቀም የሚመጣ ፍጅት እንዳለ ማንም አይጠፋውም፡፡ ለዚህ ግን መፍትሔው ማህበራዊ ሚዲያዎችን ማፈንና መንግስት የሚፈልገው ብቻ እንዲፃፍበት ማድረግ ሳይሆን ሌሎቹን በህግና በሀላፊነት ላይ የተሰማሩ የመገናኛ ብዙሃንን መደገፍና ማበረታታት ነው፡፡

በሀገሪቱ የነበሩትና ምዝገባ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ የግል የመገናኛ ብዙሃን የተለየ ድጋፍ ሳይደረግላቸው ገበያ ላይ ለመቆየት ጥረት ቢያደርጉም በመንግስት በኩል የተለየ ድጋፍ ሲደረግ አይታይም፡፡ የህትመት ሚዲያውም  በወረቀት ዋጋና በህትመት መናር ሳቢያ እየተንገዳገዱ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ፊቱን ወደ ማህብራዊ ሚዲያዎች በተለይም በወደ ፊስ ቡል ቢያዞር የሚገርም አይደለም፡፡

ነፃና ግልፅ ሚዲያ እንዲዳብርና እንዲጠነክር መንግስት በተለያዩ መድረኮች ላይ የግል የመገናኝ ብዙሃንን በማስታወቂያ ለመደገፍን ፓሊሲ እያረቀቅሁ ነው የሚል ተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቱን እናስታውሳለን፡፡በመሆኑም መንግስት ይህንን መግለጫወን ትቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገባ ይገባል፡፡

ያን ጊዜ ሃላፊነት በሚሰማቸው የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ ዜጎች ድምፅ እንዲሰማ በማድረግ የዲሞክራሲያዊ ስርዓቱ እንዲዳብር ማድረግ ይቻላል፤ አለበለዚያ ግን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እጅን በመቀሰር ችግሩን መፍታት እንደማይቻል ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe