ይልቅ ወሬ ልንገርህ – ለሠራኞች ደሞዝ መክፈል ስላቃተው የኢትዮጵያ መንግስት

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከእረፍት መልስ መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው  26ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሎው ምን ይመስል እንደነበር ሰምተሃል? አልሰማሁም፤ እንግዳውስ ልንሀገርህ፤ የፌዴራል መንግስት የ2011 በጀት ዓመት ተጨማሪ  የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል።

እንዴት አልክ? የ2011 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅን የመረመረው ምክር ቤቱ ለዝርዝር እይታ ለገቢዎች ፋይናንስ እና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራ ሲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሳለፍነው የካቲት ወር ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ለ2011 በጀት ዓመት 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ሆኖ እንዲጸድቅ ለምክር ቤቱ መላኩ ይታወሳል።

ተጨማሪ በጀቱ ክፍያቸው ላልተከፈሉ ፕሮጀክቶች ክፍያ ለመፈጸም፣ የህዝብና ቤት ቆጠራ ወጪን ለመሸፈን፣ ለቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የመንገድ ግንባታና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ወጪን ለመሸፈን፣ የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከልና ለመቋቋም እንዲሁም በበጀት አመቱ የተቀመጡ የፕሮግራም በጀት ግቦችን ለማሳካት የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

ተጨማሪ በጀቱ ካስፈለገባቸው ጉዳዮች መሀከል የፌደራል መስሪያ ቤቶች መደበኛ በጀት አንዱና ዋነኛው ሲሆን ለዚህም ለደሞዝ ክፍያ የሚሆን 23 .75 ቢሊዮን በብር ተጨማሪ በጀት ካልፈቀደ በቀር የሠራተኞችን ደሞዝ እስከ መጪው ሰኔ ድረስ ለመክፈል አስቸጋሪ ተግዳሮት መፈጠሩ ተነግሯል፡፡

የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት ለውጡን ተከትሎ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ቢሞክርም በየጊዜው ከሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ግጭቶችና መፈናቀሎች ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ መቀዛቀሩ መንግስት አስቀድሞ የያዘውን መደበኛ በጀት ለቀውሱ ለማዋል በመገደዱ የተነሳ የሠራተኞችን ደሞዝ በተጨማሪ በጀት ስም ለማስፈቀድ ሳይገደዱ እንዳልቀረ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለመንግስታቸው እንዲፀድቅላቸው ለፖርላማው አቅርበውት የነበረው የፌደራል መንግስት በጀት 346 ቢሊዮን 915 ሚሊዮን 451 ሺ 948  ብር የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 91.7 ቢሊዮን ብሩ ለመደበኛ በጀት ተይዞ ነበር፤ 113.6 ቢሊዮን ብሩ ለካፒታል በጀት የተበጀተ ሲሆን  ለክልሎች ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ አስተዳደሮች የበጀት ድጎማ 139.6 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 6 ቢሊዮን ብር ተይዞ ነበር ተብሏል፡፡

መንግስት ተጨማሪ ያቀረበው የበጀት ጥያቄ ቀደም ሲል ፀድቆ ስራ ላይ ከዋለው በጀት ጋር ሲደመር የሀገሪቱ አጠቃላይ በጀቱ  369 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ለደሞዝ ተይዞ የነበረው በጀትም ወደ 115 ቢሊዮን ብር ማሻቀቡ ታውቋል፤

ያም ሆኖ  መንግስት ”ለመደበኛ ወጪ የሚበደረው ገንዘብ ከካፒታል ወጪ መብለጥ የለበትም” ከሚለው የኢትዮጵያ የበጀት ፖሊሲ ጋር የሚጋጭ እንደሆነ በመጥቀስ ከምክር ቤት አባላት ተቃውሞ ገጥሞታል፤

አሁን የቀረበው ተጨማሪ በጀት  33 .9 ቢሊዮን ብር ውስጥ  16.9 ቢሊዮን ብሩ  ከዓለም አቀፍ ብድር የተገኘ ሲሆን ቀሪው በእርዳታ የተገኘ ነው፤ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ለዝርዝር እይታ  የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር እንዲያየው  መርቷል፤ በል ቻዎ….

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe