ይልቅ ወሬ ልንገርህ – የህግ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ከእነ ችግሩ ፀደቀ

5ኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የህግ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ለምን አስፈለገ በሚል ሰፊ ውይይት መቀስቀሱ ተሰማ፡፡ ማዕከሉን ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ እንደሚገልፀው ከሆነ የህገ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮን ተደራሽነት በማስፋጽና ህገ መንግስታዊ እሴቶችን ለማስገንዘብ ሰፊ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ እንዲሁም ከዘመኑ ስልጣኔ ጋር መራመድ የሚችል ትውልድ ለመፍጠር የሚያግዝ በመሆኑና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የምክር ቤት አባላት እንደገለፁት በመላ ሀገሪቱ ከ40 በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተገንብተው ተማሪዎችን እያስተማሩ መሆኑን በማስታወስ ትምህርቱን በአንድ ወይም እንደ አስፈላጊነት በየክልሉ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መክፈትና ተማሪዎችን ተቀብለው እንዲያስተምሩ ማድረግ እየተቻለ ራሱን የቻለ የህገ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከልን በአዋጅ ማፅደቅ ተገቢ አለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተጠሪ የሆነው ይህ ማእከልን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡ ሌላ የምክር ቤት አባል እያንዳንዱ መስሪያ ቤት እየተነሳ የትምህርት ተቋ የሚያቁም ከሆነ የሀብት ብክነት እንደሚፈጥር በመግለፅ በቋሚ ኮሚቴው በኩል እንደገና እንዲታይ ተጠይቋል፡፡ በቋሚ ኮሚቴ በኩል ታይቶ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን የጠቀሱት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሽታየ ምናለ ረቂቅ አዋጁ ለዛሬ የቀረበው እንዲፀድቅ መሆኑን በማስታወስ እንደገና ወደ ቋሚ ኮሚቴ የሚላክበት አሰራር የሌለ በመሆኑ በድምፅ ብልጫ ውሳኔ እንዲሰጥ በመጠየቅ በአብላጫ ድምፅ የማዕከሉ ማቋቋሚያ አዋጅ ከእነ ችግሩ ፀደቋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe