በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ቢበዛ ለ2 ወር ብቻ የሚበቃ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል፤

በጦርነቱ ሳቢያ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመን መቀነስ እንደ ምክንያት ቀርቧል፤

ኢትዮጵያ ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት እጇ ላይ ያለው የውጭ ምንዛሬ ቢበዛ ለሁለት ወር የሚበቃ ብቻ እንደሆነ ተነገረ፡፡

ኢትዮጵያ ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚኖራት የውጭ ምንዛሬ ቢበዛ የሁለት ወር ብቻ እንደሆነ የተነገረው የምእራባዊያን ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ጉዳዮች እና ድህረ ግጭት ላይ በተካሄደ  የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ  እንደተናገሩት ባሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት ያላት የውጭ ምንዛሬ ክምችት ቢበዛ ለሁለት ወር የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ጉዳዮች እና ድህረ ግጭት ላይ ባተኮረው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ፕሮፌሰሩ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት አንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ በእጇ ላይ ያለው የውጭ ምንዛሬ በጣም ውስን ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌ ያህልም እንደ ኬኒያ ያሉ ሀገራት ለስድስት ወር የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላቸውም ነው ምሁሩ የተናገሩት፡፡

የውጭ ምንዛሬው ዕጥረቱ በጦርነቱ እና በምእራባዊያን ተጽእኖ ምክንያት እንደተከሰተ የታገሩት ፕሮፌሰሩ በጦርነቱ እና በምእራባዊያን ትጽእኖ ምክንያት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ሊቀንስ ስለሚችል እንዲሁም እርዳታ የሚሰጡ ሀገራትም ድጋፋቸውን የሚያቋርጡ ከሆነ በከፍተኛ ሁኔታ  በውጭ ምንዛሬው ላይ ጫና ይኖረዋል ብለዋል ፕሮፌሰር አለማየሁ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe